Wednesday, January 5, 2022

በአዲስ አበባ የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲከናወን የነበረው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ

በአዲስ አበባ የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲከናወን የነበረው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ
****************************
የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ በማረም ሁለንተናዊ ድል እስከሚረጋግጥ በጦርነቱ ውስጥ የተገኙ ትሩፋቶችን  አጠናክረን ድላችንን የመጠበቅና የማስፋት ዓላማ የያዘው የውይይት መድረክ የአጠቃላይ ክፍለ ከተማና የወረዳ አመራር ውይይት ማጠቃለያ በፕላዝማ ተካሂዷል::

በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ባሉ አጠቃላይ አመራር ባለፉት ሶስት ቀናት የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ሲባል በተካሄደው ትግል የተገኙ አንጸባራቂ ድሎችን ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ እና የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በውድ ልጆቿ መስዋዕትነት ድል ያስመዘገበች በመሆኑ ይህ የተገኘውን ድል መጠበቅና ማስፋት እንደሚገባ ተገልጿል።

የማጠቃለያ ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ መምራታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon