ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች
የሽብር ቡድኑን ትሕነግና የአጋሮቹን ወንጀል ለዓለም በማጋለጥና በመሟገት የምትታወቀው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገባች።
ጋዜጠኛዋ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ አቀባበል አድርገውላታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለ1 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጅ ዲያስፖራዎች ያቀረበውን የወደ አገር ቤት ግቡ ጥሪ ተከትሎ ነው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አዲስአበባ የገባችው።
የሲቢኤስ ጋዜጠኛና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄርሜላ ከኢትዮጵያ አጀንዳነት ተሻግሮ ዓለም ዐቀፍ ንቅናቄ የሆነውን እምቢ ለባርነት ወይም የበቃ #Nomore እንቅስቃሴን በማስጀመርም ትታወቃለች።
Journalist Hermela arrives in Addis Ababa
Hermela Aregawi, a journalist known for exposing and defending the terrorist group and its affiliates, arrived in Addis Ababa this morning.
Upon arrival at Addis Ababa Bole International Airport, the journalist was welcomed by senior officials of the Ministry of Foreign Affairs and Athlete Major Haile Gebreselassie.
Hermela arrived in Addis Ababa following a call by the Ethiopian government for a homecoming of 1 million Ethiopians, Ethiopians of Ethiopian descent and friends of the Ethiopian Diaspora.
Hermesla, a CBS journalist and Ethiopian-born, is also known for launching the #Nomore movement, an international movement that has gone beyond the Ethiopian agenda.
(Pole)
(ዋልታ)
No comments:
Post a Comment