Shop Amazon

Wednesday, January 5, 2022

Members of Defend Ethiopia said that during their stay in Ethiopia, we would like to ask the embassies that disseminate false information about Ethiopia to refrain from their actions.

በአገር ቤት ቆይታችን ኢትዮጵያን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ኤምባሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥያቄ እናቀርባለን
**********************

በአገር ቤት ቆይታችን ኢትዮጵያን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ኤምባሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥያቄ እናቀርባለን ሲሉ የ”ዲፌንድ ኢትዮጵያ ” አባላት ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እየገቡ ነው።

ወደ አገር ቤት ከገቡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት መካከል በ12 የአውሮፓ አገራት በመንቀሳቀስ የኢትዮጵያን እውነት ለማሳወቅ የሚሰራው “ዲፌንድ ኢትዮጵያ” አባላት ይገኙበታል።

የቡድኑ አባላት እንደሚሉት፤ በአገር ቤት ቆይታቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ አድርገው ኢትዮጵያን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ኤምባሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀርባሉ።

በእንግሊዝ የ”ዲፌንድ ኢትዮጵያ” ተጠሪ አቶ ዘላለም ተሰማ፤ ቡድኑ የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከማሳወቅ ባለፈ አንዳንድ ምዕራባዊያን በአፍሪካ አገራት ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አካሄድ እንዲያስተካክሉ እንደሚታገል ተናግረዋል።

ቡድኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር ለመወያየት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና በዚህም ጥያቄያቸውን በአካል ለማቅረብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ውይይቱ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ኤምባሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥያቄያቸውን በጽሁፍ እንደሚያቀርቡ አብራርተዋል።

ለአሸባሪው ህወሃት ድጋፍ የሚሰጡ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና አሸባሪ ቡድኑ ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እንዲያወግዙ እንደሚጠይቁም ጨምረው ገልጸዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ያወደማቸውን አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉም እንዲሁ።

ኢትዮጵያ እየተደረገባት ያለውን ጫና በማሸነፍ ዳግም የአፍሪካ ነጻነት ምሳሌ እንደምትሆን ያላቸውን እምነት የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው የቡድኑ አባል አቶ ዘላለም ጌታሁን ናቸው።

በጀርመን አገር የሚኖሩት ወይዘሮ አስቴር ሮዝስታር በበኩላቸው አሸባሪው ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ዳያስፖራው በአገሩ ጉዳይ እንዳይሳተፍ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

አሁን ላይ ዳያስፖራው በአገሩ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በአሜሪካ ቺካጎ ነዋሪ የሆኑት አቶ የሱፍ ሃሰን፤ አገር በተቸገረችበት ጊዜ መድረስ በታሪክ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን  ተናግረዋል።

በመሆኑም ዳያስፖራው በሚችለው አቅም አገሩን መደገፍ እንደሚጠበቅበት ጥሪ አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ዳያስፖራው የገና በዓልን በኢትዮጵያ ለማክበር በስፋት ወደ አገር ቤት እየገባ መሆኑን ተናግረዋል።

ዳያስፖራው የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን  ገልጸው፤ ይህን ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
We call on embassies that disseminate false information about Ethiopia during our stay at home to refrain from their actions.
 **********************

 Members of Defend Ethiopia said that during their stay in Ethiopia, we would like to ask the embassies that disseminate false information about Ethiopia to refrain from their actions.

 Ethiopians living in different parts of the world and friends of Ethiopia are flocking home following the call of Prime Minister Dr. Abiy Ahmed.

 Among the Diaspora members are members of Defend Ethiopia, which works in 12 European countries to inform Ethiopian truth.

 According to team members:  They call on embassies based in Addis Ababa to refrain from spreading misinformation about Ethiopia.

 Zelalem Tesema, Defend Ethiopia Representative in the United Kingdom;  He said the group would not only convey Ethiopia's truth to the international community, but would also fight some Westerners to correct their misconduct in Africa.

 He said the group is working to hold talks with the ambassadors of European countries in Ethiopia and will work to make their request in person.

 If the talks fail, he said, embassies that spread false information about Ethiopia will be asked to refrain from their actions.

 He further added that those who support the terrorist TPLF should refrain from their actions and condemn the human and material damage caused by the terrorist group.

 They also support the efforts of the terrorist group to rebuild the devastated areas.

 Another member of the group, Zelalem Getahun, expressed hope that Ethiopia would once again be an example of African independence by overcoming pressure.

 For her part, Esther Rostster, who lives in Germany, said that during the TPLF regime, the Diaspora was not involved in the affairs of the country.

 He noted that the Diaspora is now actively involved in the affairs of the country.  This strengthened


No comments:

Post a Comment