Shop Amazon

Wednesday, January 5, 2022

Terrorism of the TPLF is a threat to our very existence and we must always be vigilant" - Chief Executive Officer

❝አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን የኀልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልጊዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን❞ - ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ 

*******************

አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን የኀልውናችን ስጋት በመሆኑ ሁልጊዜም በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን መጠበቅ አለብን ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ። 

ርእሰ መሥተዳድሩ  ባስተላለፉት መልዕክትኅልውናችን ለማስከበር መላ ሕዝባችን ያለምንም ልዩነት በአንድነት የከፈለው መስዋእትነት የጠላትን ወረራ መቀልበስ እንዳስቻለ ኹሉ በቀጣይም ለኅልውናችን ስጋት የሆነውን ወራሪ ቡድን ለመዋጋት ብቻ ሳይሆን ለውስጣችን ሰላምና ልማትም ወሳኝ በመሆኑ አንድነታችን አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል። 

በጦርነቱ የተዳከመውን   የከተሞቻችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ  በመጪው ጊዚያት የቱሪስት ከተማዎችን የበለጠ እንዲነቃቁ የሚከበሩ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለመሻሻል መስራት እንደሚገባም  ርዕሰ መስተዳደሩ ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል። 

ከመደበኛ አከባበሩ በተጨማሪ ዳያስፖራው ከሀገር ፍቅር ስሜት በመነጨ እያደረገ ላለው ጉብኝትና ድጋፍ ከበዓሉ ጋር ተዳምሮ የተለየ ቀለምና ድምቀት እንዳለው ማስተጋባቱም ለውስጥም ለውጭም ዘርፈ ብዙ መልእክት እንዳለው መረዳት ይገባል ብለዋል። 

በአንድ በኩል ኅልውናችን ለማስከበር ፣በሌላ በኩል የውስጥ ሰላማችንና ልማታችንን ለማፋጠን ኹላችንም እኩል ትኩረት ሰጥተን መንቀሳቀስ ይገባናልም ብለዋል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ዶ/ር ይልቃል ከፋለ።

"Terrorism of the TPLF is a threat to our very existence and we must always be vigilant" - Chief Executive Officer

 *******************

 "The TPLF invading group is a threat to our very existence and we must always be vigilant," he said.

 In his message, the President said that the sacrifices made by all our people to ensure our survival have been able to repel the enemy's invasion and that we must continue to strengthen our unity as it is important not only to fight the invading group but also to our internal peace and development.

 He also said that the economic activities of our war-torn cities should be used as an opportunity to further revitalize tourist cities in the future.

 In addition to the regular celebration, it is important to understand that the Diaspora is expressing its unique color and color to its patriotic visit and support, he said.

 "On the one hand, we must all work together to ensure our survival and accelerate our internal peace and development," said Dr. Yilkal Kefale, Chief of the Amhara Regional State.



No comments:

Post a Comment