Shop Amazon

Thursday, January 6, 2022

The Aluha Bridge, which was demolished by the terrorist TPLF, has been completed and is open for service

በአሸባሪው ህወሃት ፈርሶ የነበረው የአልውሃ ድልድይ ጥገና ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************************

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ፈርሶ የነበረው የአልውሃ ድልድይ ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ቡድኑ የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው እና ሲፈረጥጥ የአልውሃን ድልድይ አፍርሶ መሄዱ ይታወቃል።

አካባቢው ከአሸባሪው ቡድን ነጻ መሆኑን ተከትሎ የተጀመረው የአልውሃ ድልድይ የጥገና ስራ በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ኢዜአ በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል።

የአልውሃ ድልድይ ፕሮጀክት መሃንዲስ ኢንጅነር ዮሐንስ አያሌው በወቅቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የድልድዩ የጥገና ስራ በሰባት ቀናት ውስጥ ተጠናቋል።

የድልድዩ ግንባታም ሙሉ በሙሉ በብረት የተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ 55 ሜትር ገደማ ርዝመት እንዳለውም ተናግረዋል።

ድልድዩም 60 ቶን ወይም 600 ኩንታል የመሸከም አቅም እንዳለውም ጠቅሰው፤ ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት በአጭር ጊዜ ውስጥ የጥገና ስራው እንዲከናወን መደረጉን አመልክተዋል።

የድልድዩ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ የቻለውም የኮምቦልቻ ዲስትሪክት የወልድያ ሴክሽን ሰራተኞች ሌት ተቀን በቁጭት ባከናወኑት ስራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ድልድዩ ረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ጥራቱን ጠብቆ መጠገኑን ገልጸዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብና አሽከርካሪዎች በድልድዩ መልሶ መገንባትና ለአገልግሎት መብቃት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

The Aluha Bridge, which was demolished by the terrorist TPLF, has been completed and is open for service
 ***************************

 Alwha Bridge, which was demolished by the terrorist group TPLF, has been completed and is operational.

 It is known that the Alwhan Bridge collapsed when the group could not cope with the blow.

 ENA observed that the Alwaha Bridge, which started following the liberation of the area from the terrorist group, has been completed and is open for service today.

 Alwha Bridge Project Engineer Yohannes Ayalew told ENA at the time:  Repairs to the bridge were completed in seven days.

 He said the construction of the bridge was made entirely of steel.  He also said that it is about 55 meters long.

 He said the bridge has a capacity of 60 tons or 600 quintals.  He said the repair work was carried out in a short period of time due to the high cost of the service provided.

 He said the construction of the bridge was completed in a short period of time due to the hard work of Woldia Section staff of Kombolcha District.

 He said the bridge has been maintained to ensure long service life.

 The ENA reported that the local community and drivers are happy that the bridge has been rebuilt and is ready for use.




 

No comments:

Post a Comment