ታህሳስ 28፣2014
የመንግስት የልማት ድርጅቶች በአላትን አስታከው የተለያዩ ስጦታዎችን በማበርከት ሀብት እንዳያባክኑ ተከለከሉ።
የገንዘብ ሚኒስቴር ለየመንግስት የልማት ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ ነው ክልከላውን ያሳወቀው፡፡
ክልከላው ሃብትን በቁጠባ መጠቀምን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ለልማት ድርጅቶች ከተፃፈላቻ ደብዳቤ ሸገር ተመልክቷል፡፡
የልማት ድርጅቶች በአላትን እያስታከኩ አጋሮቻችን በሚል ለግለሰቦች እና ለተለያዩ ተቋማት ስጦታ የማበርከት ልማዳቸውን እንዲያቆሙ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቃል፡፡
በኮሮና በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጫና ውስጥ መሆኑን የጠቀሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጫናውን ተቋቁሞ ልማቱን ለማስቀጠል እንዲህ ያሉ ሀብት የሚባክንባቸው ልማዶችን ከማስቆም ጀምሮ የለተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈልጓል ብሏል፡፡
እንደየ ተቋማቱ ቢለያይም በተለያዩ የበዓላት ጊዜ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከስጦታ ካርድ ጋር ውስኪና ወይንን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ለግለሰቦችና ለተቋማት በስጦታ የማበርከት ልማድ እንደነበራቸው ተሰምቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የ2014 በጀትን ለመደገፍ ከውጪ ምንጮች ይገኛል ተብሎ የታሰበው ገንዘብ በዚህ ዓመት ላይገኝ ስለሚችል በጀትን ከብክነት በፀዳ መልኩ እና በቁጠባ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ለመንግስት ተቋማት ማሳሰቢያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
#Ethiopia #ShegerFM #ገንዘብ_ሚኒስቴር #በዓል #ገና #ShegerWerewoch
December 28, 2014
Public enterprises have been banned from wasting resources on holidays and donations.
The Ministry of Finance announced the ban in a letter to public enterprises.
Sheger wrote in a letter to development agencies that the ban was aimed at saving resources.
The Ministry of Finance has announced that it has decided to discontinue the practice of donating to individuals and organizations in the name of our partners during the holidays.
The letter from the Ministry of Finance stated that the Ethiopian economy is under pressure due to the war and other reasons.
Despite the differences, it is believed that during the festive period, public enterprises used to give gifts to individuals and institutions, including whiskey and wine, during the holiday season.
The Minister of Finance, Ahmed Shide, has warned government agencies that the budget, which is expected to be available from outside sources this year, may not be available this year.
Trudy Zerihun
#Ethiopia #ShegerFM #Ministry_Minister #F Holiday #Nest #ShegerWerewoch
No comments:
Post a Comment