Shop Amazon

Monday, August 28, 2023

ብዙ ደነዞች ያልገባቸው እውነታ።

 

ብዙ ደነዞች ያልገባቸው እውነታ።

አገር ማለት ህዝብ ነው ፣ መንግስት ማለት ደግሞ ህዝብን ለማስተዳድር የተሰጠ ሓላፊነት ነው። ያ ማለት መንግስት የህዝብ ተቀጣሪ ነው። ህዝብ ከሌለ መንግስት የለም። ህዝብ ከፈለገ የፈለገዉ ሰው የመንግስት ተወካይ ማድረግ ይችላል።
መንግስት የወከለው ግን ህዝብን በፈለገው መንገድ ለማስተዳደር ነው። በግድ ካልገዛሁህ ብሎ ህዝብን መቀጥቀጥ ድሮ ቀረ። ይህ ያለፈበት ስርዓት ነው።
መንግስት እና ህብ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሲሆኑ መንግስት ቋሚ ኣስተዳዳሪ ቢሆንን እንኳ የመንግስት ተወካዩ ማለትም ግለሰቡ ግን እንደ ካልሲ መቀያየር ይቻላል። ለምሳሌ መንግስት የወከለው ግለሰብ በስራው ከባለገ፣ አምባ ገነን ሆኖ ህዝብን ከበደለ ፣ ሰነፍ እና ልፍስፍ ከሆነ ወይም አገሪቷን በአንድ አድርጎ ማስተደዳር ካቃተው ህዝብና መንግስት የሾመው /የመረጠው ሰው incompetent ከሆነ ህዝብ ወይም መንግስት ሌላ ሰው መተካት ይችላል። ይህንንም ለማደረግ ሌላ ምርጫ መጠበቅ አያስፈልገውም።ለዚህ ምሳሌ የእንግሊዝን መንግስት እዪ።
ያ የተመረጠው ግለሰብ የተሰጥው አደራ ህዝብን የማስተዳደር ተግባር ጊዚያዊ ሹመት ነው።
የመንግስት ስራ የህዝብን ፍላጎት ማሟላት ብቻ ነው። መንግስት እና ህዝብ የማይነጣጠሉ ቢሆኑም መንግስትን ወክሎ የሚያስተዳድረውን ግለሰብ ህዝብ ካልፈልለገው ግን ህዝብ ከስራው ማባረር መብቱ ነው።
መንግስት ግን ህዝብን ማባረር አይችልም።
ሃቁ ይህ ነው። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል የታየው ችግር ያ ነው።
መንግስት ለአማራ ህዝብንን እንዲያስተዳድር የሾመው ግለሰብም ሆነ ፓርቲ ለህዝቡ አይመጥንም ፣ ህዝቡ አንፈልግም ነው ያለው። ያም መብቱ ነው። ግን መንግስት በግድ ውደደው ማለት አይቻልም።
ይህ ችግር ላልገባቸው ደነዞች ደግሞ በፋኖ እና በአማራ መካከል ያለውን ልዪነት ላስረዳችሁ።
ፋኖ የአማራን ብሶት የወለደው መንግስት ለመፍታት ሃቅሙ ስለሌለው አማራው እራሱ ያቋቋመው ሰላም አስከባሪ ኃይል ነው።
ይህ የሚያሳየው መንግስት የመደበው ሰው ስራውን በትክክለኛ መንገድ ስላልሰራ ህዝብ በበጎ ፍቃደኞች አማካኝነት የተመሰረተ የህዝ ዘብ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ፋኖ አማራ ነው ፣ አማራ ደግሞ ፋኖ ነው።
ሁለቱን መነጣጠል አይቻልም። ይህ "ፋኖ መንግሰት ሊገለብጥ ነው፣ ዘራፊ ነው፣ ገዳይ ነው " የሚሉትን የፈሪዎች ፕሮፓጋንዳ አትስሙ። እንዴት አማራ ፋኖ እራሱን ይሰርቃል? ይህ የህዝብን ንቃተ ህሊና ብስለት መናቅ ነው።
ታዲያ መንግስት ይህንን ችግር ለመፍታት መሞከር እንጂ ለአገር መከላከያ የአማራ ህዝብ ገብሮ እና የውጭ ምንዛሬ እስገኝቶ የአባይን ግድብ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፣ የህዝብን ደህንነት እንጠብቅበታልን ብለን ከውጭ በተገኝ $$$$ የገዛነው የጦር መሳሪያ እና ከአብራካችን የወጡትን የመከላከያ ሰራዊት አባላትን " ኑ፣ የራሳችሁን ወገን ውጉ ጠላታችሁ አናራ ነው ብሎ" brain wash ማድረግ ነውር ነው።
ፋኖ የመከላከያ ሰራዊት ጠላት ከሆነማ ምነው ትናንት ጁንታው አዲስ አበባ ሊገባ ደብረ ብርሃን ላይ ሲደርስ ያኔ የምጥ ቀን መከላከያ "ፋኖ ድረስልኝ " ብሎ የተማጸነው ተረሳ? ያኔ ለምን ፋኖ ጠላትህ ነው ተብሎ ለመከላከያ አልተነገረውም? ይህ መከላከያን መናቅ ነው።ገና ለገና የመከላከያ መሪወች ወደኋላ ሄዶ ነገሮችን ለማጤን አቅሙም ችሎታውም ስለሌላቸው መላ ጦሩን ልክ በነሱ በጥላቻ እና በብሄር በደነዘዘ አእምሮ መለካት መከላከያን ንቀትም ስድብም ነው። የመከላከያ ሰራዊት ፋኖ ማን እንደሆን ጠንቅቆ ያውቃል። ግን በመከላከያ ወስጥ ያሉ ፋኖ እና አማራ ጠል የሆኑ አባላትን መርጦ እና አሰልፎ ኢትዮጵያዎያንን መግደል ታላቅ ወንጀል ነው። ታሪክም በጥቂር መዝገብ ታስቀምጠዋለች ።
ይህ ያስተዛዝባል፣ ፋኖ ተጠቅሞበት የሚጥሉት disposable አይደለም። ፋኖ ብሶት የወለደው የአማራ/የኢትዮጵያ ተከላካይ እና ማገር ነው። መንግስት ለፋኖ ብዙ ያልከፈለው እዳ አለበት፣ ሽልማት እና የገንዘብ ድጎማው አንድ ቀን አርቆ የሚያስብ መሪ ሲመጣ መሰጠቲ አይቀሬ ነው።
ታዲያ የመንግስት ተወካዮች እራሳቸው በፈጠሩት ችግር
ፋኖን መወንጀል "ጥይት እራሷ መታ እራሷ ትጮሃለች " የሚባለው ነው።
የአማራ ህዝብ ምን እንደሚፈልግ እራሱ ያውቃል። የመንግስት ሃላፊነት
ህዝቡ የሚፈገውን ማሟላት እንጂ ለምን መብታችሁን ጠየቃችሁ ብሎ ህዝብን ማተራመስ ኋላ Sorry ያሰኛል።
ግን "ካፈርሁ አይመልሰኝ" በሚል ፈሊጥ ህዝብን ማንገላታት ነውር እና ህገ ወጥ ነው።
ሌላው ማሳሰቢያ እናንት ከሌላ ብሄር የሆናችሁ እና የአማራን መሬት እንኳ በእግራችሁ እረግጣችሁ የማታውቁ አልሁ ባዮች አፋችሁን ዝጉ።
ይህ ችግር በአማራ ህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ ችግር ስለሆነ ችግሩን መፍታት ያለበት መንግስ እንጂ የሌላ ብሄር አይደለም።
ስለዚህ በአጉል ልወደድ፣ ልወደድ በሚል ፈሊጥ አሁን በአማራ ክልል ያለውን ችግር በደመ ነፍስ ፋኖን ማጠልሸት የእናንተን የአስተዳደር የእውቀት ብስለት ማነስ የሚያሳየው ነው።
ታዲያ ህግና ስርዓት ይከበር ከተባለ ይህንን መንግስት ማስተካከል የሚችለው የአማራን ህዝን ጥያቄ መመለስ ሲችል ብቻ ነው። ግን አንዳንዶቻችሁ የመንግስት እና የፓርቲ ልዩነት ተምታቶባችዋል።
መንግስት እና ህዝብ ተደጋግፈው የሚኖሩ ሁለት ጥንዶች ሲሆኑ ፓርቲ እና የፓርቲ መሪ ደግሞ ጊዚያዊ ተወካዮች ናቸው። ታዲያ በታሪክ አጋጣሚ የአሸናፊው ፓርቲ መሪ የአገሪቱ መሪ ሲሆን ተጠሪነቱ ለመንግስት እና ለህዝብ እንጂ ለራሱ ጎሳ ወይም ፓርቲ አይደለም።
መሪ መሆን ከህዝብ የተሰጠ ጊዚያዊ ኃላፊነት ነው። ስለዚህ አንድ መሪ "ኢትዮጵያ" የምትለውን ስም ከሹመቱ ውስጥ ካስገባ የራሱን ፓርቲ እና ጎሳ ወደ ኋላ ጥሎ ኢትዮጵያ የምትለዋን ማልያ ብቻ መልበስ አለበት። ለጌጥ ሳይሆን ከልቡ። ግን ቀን ቀን ኢትዮጵያዊ ማታ ማታ ያዙኝ ልቀቁኝ ያለ የጎሳ መሪ መሆን አይደለም። ያ በህዝብ መቀለድ ነው።
ስለዚ ይህ ከጣልያን ወረራ ጀምሮ የሰርግ እና የደስት ታቦት ሲወጣ እና አውሬ እና ሌባ ሲያስቸግር በቀር ምንም አይነት የጦርነት ጥይት ጮሆበት የማያውቅ የተስላም አገር የጦርነት አውድማ አድርጎ ሀበሬው እብዳያትስ፣ ነጋዴው እናዳይነግድ ተማሪው እንዳይማር፣ ሰራተኛው እንዳይሰራ፣ ህጻናት እንደ ልባቸው እንዳይጫወቱ፣ እሩጋውያን የእመንት ተቃማት እንደ ልባቸው እንዳይሄዱ ፣ ለመንግስት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ ሳይበላ እና ሳይጠግብ ሌላውን ኢትዮጵያዊ አርሶና ግሮ፣ ጥሮ ህዝብን ባበላ እንዴት አሁን ቀየው አድባሩ የጦት አውድማ ይሁን?
ጤፍ፣ በቆሎ፣ አተር፣ ቅቤ፣ ማር፣ ወተት፣ ሰሊጥ፣ ቆዳና ሌጦ ብሎም የዋናው የኢትዮጵያ መመኪያ የአባይ ወንዝ ባለቤት፣ ለኢትዮጵያ ታላቁን የውጭ ምንዛሬ $$$ ማስገኛ የላሊበላ፣የፋሲለደስ የጢስ ኣባይ ባለቤት የሆነን ክልል የጦርነት አውድማ ማድረግ እና አንድን አካል ሲፈልጉ አጋር እና ጓደኛ ሳይፈልጉ ደግሞ በማንም ባልተጣፈረ መረን የለሽ አውደልዳይ ቅጥያ ስም እየሰጡ ህዝብን ማሽብር ምን ይሉታል? ይህ ከውጭ ወራሪ በላይ ነው።
መንግስት እውነት የኢትዮጵያ መንግስት ከሆነ ጥፋቱን አምኖ የአመርሮች ስንፈት እና ጉድለት እንዲሁም ድክመት እና ቅጥፈት ስለተፈጸመ ይቅርታ ጠይቆ ለአማራ ህዝብ ጉልበቱ ላይ ተንበርክኮ ካሳ መክፈል እና ለዚህ ችግር መነሳት ምክንያት የሆኑትን አመራሮች ለፍርድ ማቅረብ አለበት።
ይህ በትንሽ ኢትዮጵያን በማይወዱ ግለሰቦች በኣማራ ላይ ያነጣጠርወን እንግልት መንግስት ማስቆም አለበት።
ሌላው ይህ መልክት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነው። አላማውን ትንሽ ስለሳተ ሰራዊቱ የፓርቲዎች የግል ጠባቂ ሳይሆን የአገር ጠባቂ መሆን አለበት። የኢትዮጵያን ዳር ድንበት ለውጭ ወራሪ ክፍት ጥሎ
ከራስ ወገን ጋት መዋጋት ነውር ነው።
ብሎም አንድ መከላከያ የራሱን ወገን መግደል፣ ማቁሰል፣ ንብረት ማውደም ም ሆና ሌላ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማስከተል በወታደራዊም ሆነ በህዝባዊ ፍርድ ቤት ያስቀጣል።
ስለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው። መንግስት ህዝብን እንዲያስተዳድሩ በሓይል የሾማቸው ወንጀለኞች ከስልጣን አውርዶ ህዝብ ያመነባቸው እና የፈለጋችውን መሪወችን እንዲመርጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንጂ በኔ ሪዮተ አለም በግድ ካልተገዛችሁ ብሎ ህዝብን ማተራመስ ሃገራዊም አለም አቀፋዊም ወንጀል ነው።
ይህ ጉዳይ የማያገባችሁ ግለሰቦ please give me a favour stay away from it ፣just shut up.
ሰላም ለኢትዮጵያ፣ ይሆናል መስሎን አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን ሆነን ኖርን፣ አሁን ገን
"እህህ እስከ መቼ" አለች ጂጂ
ቀድሞ የተገለጸላት እሷ ብቻ ነች።
ስለዚህ ብቻችሁ እህህ ብላችሁ በሆዳችሁ የያዛችሁት ካላችሁ ተንፍሱት።


 

No comments:

Post a Comment