Shop Amazon

Friday, April 5, 2024

የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

 የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

***
ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ።
ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B21705 አ.አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት የኩላሊት ታማሚ ነው ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ሲሆን በተያዙበት ወቅት ከአምስት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፤ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት የማታለል ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ በሚያደርግበት ወቅት ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ዘገባ፡- ሳጅን ጤናው ፈጠነ
All reactions:
2.2K

No comments:

Post a Comment