አባታችን ሆይ – ካራኦኪ ጸሎት
▶ እያንዳንዱን ጽሑፍ ለመጫወት በክፍሉ ውስጥ ያለውን “Play” ይጫኑ።
በአብያተ ክርስቲያናት በጋራ በአማርኛ ሲጸለይ ከጥቃቅን ልዩነቶች ጋራ እንዲህ ነው፦1. አባታችን ሆይ (በአማርኛ)
አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኅይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን!
2. አቡነ ዘበሰማያት (ግእዝ)
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፣ ትምጻእ መንግሥትከ፣ ወይኩን ፈቃድከ ፣ በከመ በሰማይ፣ ከማሁ በምድር። ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሃበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ፣ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፣ ኣላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኩሉ እኩይ። እስመ ዚኣከ ይእቲ መንግሥት፣ ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም፣ አሜን።
3. በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል (ግእዝ)
በሰላመ፣ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፣ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣ ድንግል ብኅሊናኪ ፣ ወድንግል በሥጋኪ። እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ። ቡርክት አንቲ እምአንስት፣ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ። ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ፣ እግዚአብሔር ምስሌኪ። ሰአሊ ወጸልዪ ምሕረት በእንቲኣነ፣ ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
4. በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል (በአማርኛ)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፣ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ። በሀሳብሽ ድንግል ነሽ ፤ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። አሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና። ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን እና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችን ይቅር ይለን። ለዘለዓለሙ አሜን።
5. የ፫ እግዚአብሔር ጸጋ
የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ። አሜን።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.