Shop Amazon

Saturday, July 15, 2017

Ha Hu and it's meaning

#ETHIOPIA | የሚደንቅ! ... ስንቶቻችን እናውቃለን?

  * እነሆ ትርጉማቸው ...

ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት
ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ
ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት
ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡
ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡
የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡
ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዪ ማለት መስተሥርዪ ማለት ነው፡፡
ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡
ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡
ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ
መለኮቱ ማለት ነው፡፡
ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡
ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡
ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡
ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡
ዶ ማለት ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ ማለት ነው፡፡
ገ ማለት ገባሬ ሰማያት ወምድር ማለት ነው፡፡
ጉ ማለት ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ ማለት ነው፡፡
ጊ ማለት ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጋ ማለት ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጌ ማለት ጽጌ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ግ ማለት ሐጋጌ ሕግ ማለት ነው፡፡
ጐ ማለት ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጒ ማለት ጒንደ ሐረገወይን ወልድ ማለት ነው፡፡
ጓ ማለት ዕጓለ እመሕያው ማለት ነው፡፡
ጔ ማለት ዝንጓጔ መስቀል ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጠ ማለት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጡ ማለት ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጢ ማለት መያጢሆሙ ለኃጥአን ማለት ነው፡፡
ጣ ማለት የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ ማለትነው፡፡
ጤ ማለት ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጥ ማለት ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጦ ማለት ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ማለት ነው፡፡
ጰ ማለት ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጥድቅ ማለት ነው፡፡
ጱ ማለት ኮጱ መዓዛ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ጲ ማለት ሠራጲሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ጳ ማለት ጳጳስ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ጴ ማለት አክራጴ ኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጵ ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው፡፡
ጶ ማለት ጶሊስ ማለት ነው፡፡
ጸ ማለት ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፀ ማለት ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጹ ማለት ገጹ ለአብ ማለት ነው፡፡
ፁ ማለት ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት ማለት ነው፡፡
ጺ ማለት ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን ማለት ነው፡፡
ፂ ማለት መላፂ ዘክልኤ አፉሁ ማለት ነው፡፡
ጻ ማለት ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፃ ማለት ፋፃ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ጼ ማለት አዕቃጼ ሰኮና ማለት ነው፡፡
ፄ ማለት ሕፄሁ ለዳዊት ማለት ነው፡፡
ጽ ማለት ጽንሁ ተስፋሁ ማለት ነው፡፡
ፅ ማለት ዕፅ አብርሃም ዘሰፀረ ለምስዋዕ ማለት ነው፡፡
ጾ ማለት ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ ማለትነው፡፡
ፆ ማለት ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን ማለት ነው፡፡
ፈ ማለት ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ፉ ማለት ምዕራፉ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ፊ ማለት ፊደለ ወንጌል ዘአባ ኀነፊ ማለት ነው፡፡
ፋ ማለት አልፋ ወኦ ማለት ነው፡፡
ፌ ማለት ኀዳፌ ነፍሳት ማለት ነው፡፡
ፍ ማለት ፍኖት ለኀበ አቡሁ ማለት ነው፡፡
ፎ ማለት ፎራ ኅብስተ ቍርባን ማለት ነው፡፡
ፐ ማለት ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፑ ማለት ኖፑ አስካለ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ፒ ማለት ፒላሳሁ ማለት ነው፡፡
ፓ ማለት ፓንዋማንጦን ማለት ነው፡፡
ፔ ማለት ፔ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፕ ማለት ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፖ ማለት በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
ወበደኃሪ የኀልፎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
የፊደላትን ትርጉም በአግባቡ ከተረዳን በዝተዋል ይቀነሱ
የሚሉትን ሰዎች ማስረዳት ከመቻላችንም በላይ ፊደላትን
ያለቦታቸው ከመጠቀም እንቆጠባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!

***
ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ ግእዝ ይትማህሩ
ወጣቶች የግእዝን ቋንቈ ይማሩ ዘንድ ወደዱ።
***
ምንጭ: ድረ ገጽ

Wednesday, March 15, 2017

ቆሼ: የአዲስ አበባ ልጆች የደበቁን ታላቁ የዘመናችን ሚስጢር

በቅድሚያ  የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ  የአዲስ አበባ ልጅ አይደለሁም። ግን ዘመድ ወዳጆቼ፣ ጓደኞቼ  ለሎች  ሌሎችም  የአዲስ አበባ ልጆች ናቸው።  አዲስ አበባ  እኔም ከተወለድሁባት ከተማ  ቀጥላ   የራሴ  ከተማ  ናት ።  በተጨማሪ  ደግሞ  አዲስ  አበባ  የእማማ ኢትዮጵያ ዋና  ከተማ ስለሆነች የሁላችንም  ከተማ ናት ።

እኔን የገረመኝ  ግን  የአዲስ አባባ  ልጅ   ሁሉ  መለያው  ሰፈሩ ነው ።   በቃ  አዲስ አበባ  በሰፈር በሰፈር ተከልሎ  እዚ  አሜሪካ  እንኳ  ጓደኛ  የሚሆነው በሰፈር ልጅ  ነው ።   ሁሉም  ጎጡ ጎጡን  ለይቶ  ነው ያለው። የፒያሳ ልጅ ፣ የቦሌ ልጅ ፣ የአራት ኪሎ፣  የአምስት ኪሎ፣ የመርካቶ፣የአዲስ ከተማ ፣የካዛንችስ፣ የቄራ፣ የፈረንሳይ ፣የጉለሌ  ሌላም ሌላም።  ሁሉም   የየራሱን   ሚና  ለይቶ  ያራሱን  ሰፈር ሲክብ፣ሲያሽሞነሙን፣ ከኔ በላይ አራዳ፣ ጨላጣ  የለም እያለ  የራሱን  ሲያስበልጥ  ይህው ከግማሽ  ምእተ አመት በላይ በዚህች  ምድር ላይ  ስኖር  አንድም  ሰው ስለ ቆሼ  ተንፍሶ አያውቅም ። አንድም  የአዲስ አበባ ልጅ  ስለ  ቆሼ ልጆች ተንፍሶ አያውቅም።

ሁሌ  የምሰማው  የኛ  ሰፈር ፎቅ ተሰራ፣ቀለበት  መንገድ በዚህ አለፈ፣በዚህ ተጠለፈ፣ጁስ ቤት፣ማሳጅ ቤት፣ ሆቴል፣ናይት ክለብ፣ ጫት ቤት፣ሁካ  ቤት  ወዘተ  ነው።

አይ  ቆሼ  ሰፈር?  ከብዙ  አመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ  ቆሻሻ  ሲጣል በጣም  ብዙ  ህዝብ ከቦ በቆሻሻው ሲሻማ  የሚያሳይ ቪዲዮ  ኢንተር ኔት ላይ አይቼ በጣም  አዝኜ  ነበር፣  ግን  ያ ቪዲዮ  የትና  መቼ  እንደተቀረፀ አላውቅም ።  ከዚያ  በቅርብ  አንድ  ፊልም  በYoutube ተመለከትሁ ፣ የፊልሙ እርእስ  “የቆሼ  ልጅ  ” ይላል።  ያንን  ቪዲዮ  አይቼ  በጣም   አዝኘ እና ተደንቄ  ለአንዱ ስነግረው “ ይገርምሃል ያንን  ፊልም  ልክ ቦታውን  እና ሰወችን  ነው ያሳዩን ” አለኝ
 ”እኔ እኮ  ልብ  ወለድ መስሎኝ  ነበር?“ ስለው
“ልብ  ወለድ አይለም እውነት ነው” አለኝ

ከዚያ  ለሌሎች  የአዲስ  አበባ ልጆች  ስነግራቸው ለካን ይህ  የአደባባ ሚስጢር ኖሯል።  ሁሉም  ያውቁታል ።  ለካን የቤት ጉድ  የሚሉት  አይነት ሆኖ  ተከድኖ  ይብሰል አይነት ሆኗል።  ለካን ቆሼ  የአዲስ  አበባ  የተደበቀሽ ሚስጢር ኖራለች።

ለካን ቆሼ  አለም ሳያውቃት ተደብቃ  የምትኖረ  የአዲሰ  አበባ ሚስጢር ኖራላች።
ለመሆኑ  የቆሼ  ልጆች  ዲቪ አይደርሳቸውም?  አሜሪካ  ሰው አያስመጣቸውም?  ወይስ  እነሱም  የቆሼ ልጅ ነኝ ብሎ  መናገር  ትንሽ  ከበድ ስለሚል  የሌላ  ሰፈር ልጆች ነን ይላሉ?

ዛሬ ያ  ሁሉ  ሚስጢር ቧ  ብሎ ተከፍቶ  አለም ቆሼን በቴላቭዥኑ መስኮት እያያት ነው።

ቆሼና  የወሎ እርሃብ  ተመሳሳይነት አላቸው፣ ሁለቱም  ለ አለም ህዝንእይታ  ተደብቀቅ  ባጋጣሚ  የቴለቭዥን  መስኮት ህዝብን  ያሳዘና  እና  ያስለቀሰ እይታዎችን  ይዘው ቀርበዋል።

ግን  ማነው ተጠያቂው? 100% መንግስት ነው ። መጀመሪያ  ደረጃ  ህዝቦች  ለጤናቸው ሲባል የህዝብ  ቆሻሻ  ከሚጣልበት አካባቢ መድረስ  የለባቸውም ።  ምክንያቱም  በዚህ  ቆሻሻ  መጣያ  ቦታ  ከሆስፒታሎች  እና  ከተለያዪ  ቦታዎች የሚመጡ  መርዞች እና በበሽታ የተበከሉ እቃወሽ  ስለሚኖሩ  ከዚያ  የሚመጣው በሽታ  ለግለሰቡ ብቻ ሳይሆን  ለሌላውም ህዝብ  ሊተላለፍ ስለሚችል  መንግስት  የሚጣለውን  ቆሻሻ ማንም ሰው  እንዳይደርስበት በ እጥርና  በዘበኛ  መጠበቅ ነበረበት።  ከቆሻሻው የሚገኘውን  ነገር መልሶ  ለመጠቀም  ወይም  ሪሳይክል ለማድረግ  ቢፈለግ  በህግና  በስነ
 ስርዓት ፈቃድ ያለው ድርጀት  ህዝቦችን  ቀጥሮ  ማሰራት ይችል ነበር።

ግን  መንግስትም ዝም  ህዝቡም ዝም ብሎ  የቆሼን  ህዝብ  በሚስጢር ይዞ መንቀሳቀሱ  እንደ
 አማራጭ  ተወስዶ  ዛሬ  ቆሼ  የሬሳ አውድማ  ሆናለች።  የሚያሳዝነው በሂወተ  ያሉትስ  የቆሼ  ነዋሪወች  ስንቱ ይሆን በበሽታ የተለከፈው ?ስንቱ ይሆን  የቁም  ሙት የሞተው?
ቆሼ የአዲስ  አባባ  ሚስጢር

ያሳዝናል::
በአንድ ከተማ  ሁለት ዜጎች 

     

አትላንታ ሴት ልጁን የገረዘው ኢትዮጵያዊ የአስር አመት እስሩን ጨርሶ ወደ የኢትዮጵያ ተጠረዘ

Father Imprisoned for Genital Cutting Is Deported to Ethiopia
Khalid Adem in 2006.

JASON BRAVERMAN / GWINNETT DAILY POST, VIA ASSOCIATED PRESS

By DANIEL VICTOR

MARCH 14, 2017
A man who in 2006 became the first person in the United States to be convicted of female genital cutting was deported on Monday to his home country, Ethiopia, after serving 10 years in prison, federal authorities said.

The man, Khalid Adem, 41, used scissors to remove the clitoris of his 2-year-old daughter in his family’s Atlanta-area apartment in 2001, prosecutors in Gwinnett County, Ga., said. He was convicted of aggravated battery and cruelty to children.
The case led to a state law prohibiting the practice, which was already prohibited by a federal law and is a common social ritual in parts of the world but is broadly condemned.
“A young girl’s life has been forever scarred by this horrible crime,” Sean W. Gallagher, a field office director for Immigration and Customs Enforcement, said in a statement on Tuesday.
“The elimination of female genital mutilation/cutting has broad implications for the health and human rights of women and girls, as well as societies at large.”
The World Health Organization has estimated that more than 200 million girls and women have been cut in 30 countries, mostly in Africa, the Middle East and Asia. The procedure, which involves the removal of parts of the genitalia, is typically performed on girls before they turn 15 and leads to a wide range of lifelong health consequences, including chronic infection, childbirth complications, psychological trauma and pain during urination, menstruation and intercourse.
The practice is far from unheard-of in the United States. Though it is illegal under federal law, about half a million women have undergone the procedure or are likely to be subjected to it, according to a 2012 report by the Centers for Disease Control and Prevention.
Cutting has presented new challenges for doctors as the number of African immigrants in the United States has grown. In 2013, lawmakers extended the federal ban to include “vacation cutting,” in which American-born girls are sent to other countries to have the cutting performed.
I.C.E. has arrested at least 380 people and has deported 785 known or suspected human rights violators since 2003, the agency said.
In 2016, Unicef said the rate of cuttings had declined over three decades, with adolescents about one-third less likely to be cut than 30 years ago.
Customs are changing in some counties where the practice used to be widespread. In 2015, a doctor in Egypt became the first person in that country to be convicted of the practice. Somalia’s prime minister signed a petition in 2016 that called for his government to ban it. The country of Georgia outlawed genital cutting in January.