እንደ ኢትዮጵያዊ እግዚያብሔርን በየ ሰአቱ የሚጠራ የለም::
እኛ ኢትዮጵያዊያን እግዚያብሔርን ሳናውቅ በቃ በክፉም በደጉም እናነሳዋላን ግን አይታወቀንም
ለምሳሌ
ሰላም ነው ሲል ይመስገን
ሰው ሲያስንጠሰው ይማርህ
ከተጎዳን ይብስ አያማጣ
አንድን ሰው ከጠላንው ይድፋህ
ተንኮለኛውን የጅህን ይስጥህ
ያታለለን ያሳየኛል
ከከፋን እስኪ አንተ ታውቃለህ
ከጨነቀን ያዛሬን አውጣን
ከቸገረን እረ ሙላበት
ካመመን እረ ፈውሱን ላክ
ሰው ሙዝዝ ካለብን እረ ገላግልን
ያልሆን ነገር ስናይ ምኑን ጣለብን?
ሌላም ...
ታዲያ እግዜር እኛን ያልሰማ ማንን ይስማ?
አልሰማም ያላችሁ ካላችሁ እንዳትሞኙ ቀኑን ጠብቆ ይመጣል ሁሉም ለደግ ነው።
አሜን
No comments:
Post a Comment