Shop Amazon

Thursday, October 22, 2020

እውነተኛውን የብር ኖት ከሀሰተኛውን እንዴት መለየት ይችላሉ?

እውነተኛውን የብር ኖት ከሀሰተኛውን እንዴት መለየት ይችላሉ?

• የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ፡፡
• የብሩን ዋጋ የሚገልጽ፤ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ አለው፡፡
• የብር ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት አለው፡፡
• ገንዘቡ ወደላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ ይታያል፡፡
• የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE፣ ኢብባ እና የገንዘብ አይነት ተጽፎ ይገኛል፡፡
• ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል፡፡
• የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘቡ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍጹም ትይዩ ሆነው በአንድ ላይ ያርፋሉ፡፡
• አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፊሎረሰንት ምልክት እንዳለው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

No comments:

Post a Comment