Shop Amazon

Thursday, October 22, 2020

ከ2 ሚሊዮን በላይ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የገንዘብ ዝውውር መመሪያን በመተላለፍ በግለሰብ ቤት ውስጥ
የተከማቸ ከ2 ሚሊዮን በላይ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
******************
ወቅታቂ የገንዘብ ዝውውርን አስመልክቶ የባንክ አዋጅ 591/2008 እንደሚያስረዳው በአንድ ግለሰብ እጅ መገኘት ያለበት የብር መጠን 1.5 ሚሊዮን እና ከዚያ በታች ሲሆን ይህንን ተላልፎ ከተጠቀሰው የብር መጠን በላይ ይዞ የተገኘ ግለሰብ ገንዘቡ እንደሚወረስ በግልጽ ተቀምጧል ፡፡ 
 ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዶምቦስኮ ት/ቤት አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ  ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ቲም ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ይርጋ ተካ እንደገለፁት በህዝብ ጥቆማ የተያዘው 2 ሚሊዮን 222 ሺህ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር የዋለው  የብሄራዊ ባንክ መመሪያን በመተላለፍ በግለሰብ እጅ መገኘት ከሚፈቀደው በላይ ሆኖ በመገኘቱ ነው።
ህብረተሰቡ የገንዘብ ዝውውር መመሪያውን በመተግበር ተባባሪ እንዲሆን እና መመሪያውን በመተላለፍ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን እንዲጠቁም ምክትል ኢንስፔክተር ይርጋ ተካ  ይርጋ ተካ አሳስበዋል።
ዘገባ ፡- ኮንስታብል ኤቢሳ ጅሩ

No comments:

Post a Comment