Shop Amazon

Thursday, November 12, 2020

የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ

የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ 
*************************  

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛን በመጥለፍ እና የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ፣ ዕዙ በጁንታው የሕወሓት የጥፋት ቡድን ጥቃት እንዲፈፀምበት ሲያመቻቹ ተገኝተዋል በሚል የጠረጠራቸውን 7 የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል። 

ጄኔራል መኮንኖቹ በሀገር ክህደት እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድ ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል። 

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ  በእነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) መዝገብ የሚጠሩ 7ቱን ተጠርጣሪዎች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል። 

የወንጀል ምርመራ ቢሮው ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ለሚገኘው የማፊያው ሕወሓት ቡድን አመራሮች መረጃ በመስጠት እና ተልዕኮ በመቀበል የሬዲዮ መገናኛውን በመጥለፍ ሠራዊቱ እርስ በእርሱ እንዳይገናኝ በማድረግ ሀገር የማፍረስ ወንጀል ሠርተዋል በሚል ጠርጥሯቸዋል። 

እንደ ምርመራ መዝገቡ ተጠርጣሪዎቹ ይህንን ድርጊት በመፈፀማቸው በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኅልፈት እና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል እንዲሁም ከባድ የንብረት ውድመት ደርሷል። 

በእነዚህ እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል። 

ተጠርጣሪዎቹ የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈፀምንም ሲሉ ተከራክረዋል። 

ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤቱ የወንጀሉን ውስብስብነት እና ክብደት እንዲሁም በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ከግምት በማስገባት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል። 

የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። 

በጥላሁን ካሳ
 Seven generals accused of hacking a North Eastern radio station have appeared in court
 ***************************

 The Federal Police Commission (FPC) has arraigned seven general officers on suspicion of plotting to assassinate a member of the TPLF in June.

 The generals are suspected of treason and violating the constitutional order.

 The Federal Police Commission's Criminal Investigation Bureau has summoned the seven suspects in the case of M / J Gebremedhin Fekadu (Wedi Necho) to the Arada Division I Criminal Court of the Federal Court of First Instance.

 On October 24, 2013, the Bureau of Investigation (FBI) suspected that the suspects had committed a crime of subversion by providing information and commissioning to the Mafia TPLF leaders in Mekelle, intercepting a radio station and disconnecting the army.

 According to the investigation, several members of the Defense Forces were killed and maimed, and property was severely damaged.

 Police have requested an additional 14 days of investigation into these and other related crimes.

 The suspects pleaded not guilty to the charges.

 Considering the complexity and severity of the crime and the serious damage to national security, the court granted the police an additional 14 days.

 He has rescheduled the hearing for November 17, 2013.

 Compensation in the shadows



No comments:

Post a Comment