****************************************
ዘራፊው የህወሓት ቡድን “የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጀት ተደብድቧል” በማለት ያናፈሰው ወሬ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
አጥፊው የህወሓት ቡድን መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጀት ተደብድቧል ሲሉ ትናንት ምሽት የራሳቸው ልሳን በሆነው ሚዲያ ገልፀዋል።
የስኳር ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ደምሴ በወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ላይ በመንግስት የጦር ጀት ድብደባ ተፈፅሟል ተብሎ በዘራፊው የህወሓት ቡድን የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት በስኳር ኮርፖሬሽን የሚተዳደርና ንብረትነቱም የፌዴራል መንግስት መሆኑን ጠቅሰው የደረሰበት ጉዳት አለመኖሩን ለኢዜአ አስታውቀዋል።
የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በዓመት አራት ሚሊዮን 840 ሺህ ኩንታል ስኳርና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል እንዲያመርት ታቅዶ በ2009 ዓ.ም ነው ግንባታው የተጀመረው።
ይሁን እንጂ ፋብሪካው በታቀደለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ከመዘግየቱ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታ አሳድሯል።
The report that “Wolkait Sugar Factory was hit by a jet” is untrue: Sugar Corporation
*******************************************
The TPLF's rumor that the Wolkait Sugar Factory was hit by a war jet is false propaganda.
Debre Tsion Gebremichael, the leader of the destructive TPLF group, was shot dead by the Wolkait Sugar Factory in his own language last night.
Abraham Demissie, Deputy Chief Executive of the Sugar Corporation's Project Sector, has confirmed that rumors of a TPLF jet strike at the Wolkait Sugar Factory are untrue.
He said the Wolkait Sugar Factory project is managed by the Sugar Corporation and is owned by the federal government.
The construction of Wolkait Sugar Factory is expected to produce four million 840 thousand quintals of sugar and 41 million 654 liters of ethanol annually.
However, local residents complained that the factory was not completed on time.
Explaining the reason for the delay, the Deputy Chief Executive said that the feasibility study was conducted after a decision was made by the ruling party.
He said the corporation was under the influence of the same group, adding that it was not suitable for sugarcane cultivation.
ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው ፕሮጀክቱ የዘገየበትን ምክንያት ሲያስረዱ የአዋጭነት ጥናት ተጠንቶ ችግሮች እንዳሉበት እየታወቀ በወቅቱ ስልጣን ላይ በነበረው አካል ውሳኔ ተሰጥቶበት ወደ ስራ በመግባቱ መሆኑን ይገልፃሉ።
ኮርፖሬሽኑ በዚሁ ቡድን ተጽዕኖ ውስጥ የነበረ በመሆኑ ለአገዳ ልማት የውሃ አማራጭ ምቹ አለመሆኑ እየታወቀ ወደ ስራ መግባቱና የዲዛይን ችግሩ ለመዘግየቱ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል።
No comments:
Post a Comment