********************
መንግስት በህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ላይ የጀመረውን ህግ የማስከበር ርምጃ በህግ ተጠያቂ እስከ ማድረግ እንዲዘልቅ የአማራ ምሁራን መማክርት ጠይቋል።
ለሁለት ቀናት የዘለቀውን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያካሂድ ቆይቶ፣መማክርቱ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
“ኢትዮጵያ እና አማራ ጠል” የሆነውን የሕወሓት ሕገ ወጥ ቡድን ድርጊቱን እንደሚኮንነው መማክርቱ በመግለፅ ፣ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በአሸባሪነት እንዲፈረጅም ጠይቋል።
በመንግስት እየተካሄደ ያለው የህግ የማስከበር እርምጃ እንዲሁም በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት እንደሚያደንቅ እና እንደሚደግፍም አመልክቷል።
መማክርቱ ዓመታዊ የእቅድ ክንውኑ ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን በቀጣይ እቅዶች ዙሪያም መክሯል።
የአማራ ክልል ተቋማትን በሁሉም ዘርፎች ለመገንባት እና በጥናት የተለዩ ችግሮችን የያዘ የመፍትሔ ሀሳብ በጉባኤው ቀርቧል።
የክልሉን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የመፍትሔ ሃሳቦች ይሆናሉ ያላቸውን የጥናት ውጤቶችም አስቀምጧል።
የአረንጓዴ አሻራ ጅምሮች በሳይንሳዊ መንገድ ማስቀጠል የሚያስችሉ ሳይንሳዊ የሙከራ ስራዎችን መለየቱንም እንዲሁ።
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተገቢው ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ውክልና ያገኙ ዘንድ ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ተግባራትን ለይቶ አቋም መያዙን መማክርቱ በሰጠው መግለጫው አስታውቋል።
በእስሌማን አባይ
my translation.
Amhara scholars seek advice to classify extremist TPLF as terrorists
********************
Amhara scholars have called for the government to continue its crackdown on illegal TPLF groups.
Following the two-day annual general assembly, the council issued a statement.
The council condemned the TPLF's illegal activities in Ethiopia and Amhara, and called for the extremist TPLF to be classified as a terrorist group.
He expressed his appreciation and support for the government's ongoing law enforcement efforts and efforts to hold it accountable.
The council discussed the annual plan in detail and discussed future plans.
The conference proposed solutions to the construction of institutions in the Amhara region in all sectors and identified specific problems.
He also outlined the findings of research that could be a solution to improve the quality of education in the region.
It also identifies scientific experiments that can continue the green footprint in a scientific way.
The council said in a statement that it has identified the issues that need to be considered in order for the Amhara people living outside the region to receive appropriate political and administrative representation.
By Islam Nile
No comments:
Post a Comment