ህዳር 7፣2013
ዛሬ በአዲስ አበባ ፒያሳ ደጎል አደባባይ የተፈጠረው ምንድን ነው?
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፦
በአራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ደጎል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ ፈንጂ አመከነ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ፡፡
ዛሬ ህዳር 7፣2013 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደጎል አደባባይ አካባቢ ከሰዓት በፊት በጎዳና ላይ ተዳዳሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በማዕድን ውኃ መያዣ ላስቲክ ድራፍት በመግዛት ለመጠጣት ወደ አንድ ጥግ መሄዱ ያጠራጠራቸው በአካባቢው በጫማ መስዋብ ሥራ ላይ ተሰማሩ ወጣቶች ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ የአካባቢው ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ በመገኘት ተከሰተ የተባለውን ማረጋገጥ መቻላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር አካባቢያቸውን በንቃት የሚጠብቁ ወጣቶች መበራከታቸው የሚደነቅ ቢሆንም ለፖሊስ የሠጡትን መረጃ በመንተራስ ፖሊስ ባረጋገጠው መሰረት በላስቲክ የተሞላ ድራፍት ቢራ እንጂ ፈንጂ አለመሆኑን ህብረተሰቡ እዲገነዘብ ኮሚሽኑ አሳስቦ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
No comments:
Post a Comment