ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ
******************
Ethiopia, Israel agree to work together on information and security
******************
Ethiopia and Israel have agreed to work together in the information and security sector, according to the National Intelligence and Security Service.
Israeli Deputy Minister of Security Gadi Yvirkan met with Director General of the National Intelligence and Security Service Demlash Gebremichael.
During the meeting, the two countries agreed to work together to fight terrorism, exchange information, transfer technology and build capacity in the Horn of Africa.
"Ethiopia and Israel can work together in the information and security sector to strengthen peace and stability in the Horn of Africa," he said.
For his part, Deputy Foreign Minister Gadi Yvirkan said Ethiopia wants to further strengthen its cooperation with Ethiopia in the information and security sector as it has a significant role to play in maintaining peace and stability in the Horn of Africa.
He also said that Israel supports the change initiated by Ethiopia in the information sector.
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ ተባብረው ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የእስራኤል ደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ኮሚሽነር ደምላሽ ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱ አገራት በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት፣ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዘርፍ ይበልጥ ተባብረው ለመሥራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፉ ተባብረው ቢሠሩ በአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢው ሰላም እና መረጋጋት በማጠናከር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ ሲሉ ኮሚሽነር ደምላሽ በውይይቱ ገልጸዋል።
ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላም እና መረጋጋት በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና ያላት እና ተሰሚ በመሆኗ ምክንያት እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር በመረጃ እና ደህንነት ዘርፉ ያላትን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በመረጃ ዘርፍ የጀመረችውን ለውጥ እስራኤል እንደምትደግፍም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በመረጃ እና ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የደረሱትን ስምምነት በቅርቡ ወደ ተግባር ይሸጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የላከው መረጃ አመልክቷል።
No comments:
Post a Comment