Sudan says it is tightly controlling its border with Ethiopia via Kesela
Fesah al-Rahman al-Amin, the governor of Kesela state, said security forces have been beefed up in Sela State, one of Sudan's borders with Ethiopia.
This decision was made in light of the Ethiopian government's response to the TPLF.
He also said that the security forces in the area have been instructed to keep the border vigilant and prevent any individuals or groups from entering Sudan with weapons.
He also said that the force at Wade al-Helio, near the border, had been instructed to study the situation.
However, in order to receive the innocent citizens who come to Sudan seeking asylum; With this in mind, a special committee has been appointed to assist in the execution of orders, he said.
Source: Al-Sudani
ሱዳን በከሰላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበሯ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች መሆኗን ገለፀች
***************************************************
የከሰላ ግዛት አስተዳዳሪ ፈታህ አል ራሀማን አል አሚን እንዳስታወቁት ከዛሬ ጀምሮ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ከምትዋሰንባቸው ድንበሮች አንዱ በሆነው ከሰላ ግዛት አካባቢ ያለው የድንበር ጥበቃ በፀጥታ ኃይሉ እንዲጠናከር ተደርጓል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው የኢትዮጵያ መንግስት በሕወሐት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከግምት በማስገባት ነው።
በአካባቢው ያለው የፀጥታ ኃይል ድንበሩን በንቃት እንዲጠብቅና ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የጦር መሳርያ ይዞ ወደ ሱዳን እንዳይገባ እንዲያደርግ መታዘዙንም አስተዳዳሪው ፈታህ አልራሃማን ተናግረዋል።
በድንበሩ አቅራቢያ ባለችው ዋድ አል ሄሊኦ ያለው ኃይል ሁኔታዎችን በደንብ እንዲያጠና መታዘዙንም ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ጥገኝነት ፈልገው ወደ ሱዳን የሚመጡትን ንፁሃን ዜጎች ለመቀበል እንዲቻል፤ ይህን ከግምት ባስገባ መልኩ ትዕዛዞች እንዲፈፀሙ ይረዳ ዘንድ ጉዳዩን የሚከታተል ልዩ ኮሚቴም መሰየሙን አስተዳዳሪው አስታወቀዋል።
ምንጭ:- አልሱዳኒ
No comments:
Post a Comment