Shop Amazon

Sunday, November 15, 2020

The Turkish government understands that what Ethiopia is doing is a law enforcement campaign: Turkish Foreign Minister

የቱርክ መንግስት ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው ተግባር ህግን የማስከበር ዘመቻ እንደሆነ ይረዳል-የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
****************************
ቱርክ ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው ተግባር ህግን የማስከበር ዘመቻ አድርጋ እንደምትገነዘብ  የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሱግሉ (Mevlut Cavusoglu) አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሱግሉ (Mevlut Cavusoglu) በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር ሥራ  በሚመለከት በስልክ ተወያይተዋል።

ዘመቻውም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ እና መንግስት የንጹሃን ዜጎች ደህንነትን እንደሚያስጠብቅ እምነታቸው  መሆኑን የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ስለፈፀመው ጥቃት እና ዝርፊያ ገለጻ  አድርገውላቸዋል።

የጁንታው ድርጊቱ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሀገር ሉዓላዊነትን መዳፈር እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል። 

ስለሆነም ወንጀለኛውን ቡድን ወደ ፍርድ በማቅረብ በክልሉ የህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

The Turkish government understands that what Ethiopia is doing is a law enforcement campaign: Turkish Foreign Minister
 *******************************
 Foreign Minister Mevlut Cavusoglu has said that Turkey recognizes Ethiopia's actions as a law enforcement operation.

 Deputy Prime Minister and Foreign Minister Demeke Mekonnen and Turkish Foreign Minister Mevlut Cavusoglu had a telephone conversation over ongoing law enforcement activities in Tigray State.

 He said the campaign is expected to end soon and that the government will ensure the safety of innocent people.

 Foreign Minister Demeke Mekonnen briefed them on the TPLF's attack on the Northern Command.

 He emphasized that the decision was not a crime but a violation of the sovereignty of the country.

 Foreign Affairs Minister Demeke Mekonnen said law enforcement activities are underway in the region to bring the perpetrators to justice.

No comments:

Post a Comment