Shop Amazon

Thursday, December 10, 2020

አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤

“አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን  ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው፤ ቦታው ላይም ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” - ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን
************************* 
(ኢ ፕ ድ) 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን አመቱን ሙሉ በተለያቱ መድረኮች እያከበረ ይገኛል። የበአሉ አካል በማድረግም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የምስጋና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዚሁ መርሀ ግብር ላይም ወደ ግንባር ከተላኩ ጋዜጠኞች መካከል የማይካድራውን ጭፍጨፋ በስፍራው ተገኝቶ የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን የተመለከተውን ለእለቱ ታዳሚያን አጋርቷል። 

አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለው፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን  ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው ቦታውም ላይ ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” ሲል ነው ጋዜጠኛ ወንድአጥር ምልከታውን ያጋራው።

የተመለከትኳቸው ነገሮች የሚያሙ ናቸው፤ እነዚህ ህመሞች እኛን አመው ባይቆሙ ኖሮ ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፤  እውነት ለመናገር የማይካድራ ህዝብ ህመሙን ባይችለው ኖሮ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፡፡ 

ጋዜጠኛ ወንድአጥር በእለቱ በሰጠው የአይን ምስክርነት ላይም ያነሳቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፤ 

👉በማይካድራ ላይ የሞተው በዋናነት አማራ ይሁን እንጂ ኦሮሞም ሞቷል፤ ወላይታም ሞቷል፤ ሶማሌም ሞቷል፤  

👉ትህነግ ለማንኛውም ነገር እንደማይመለስ የስለት ጫፍ ድረስ ከመጨከን ወደኋላ እንደማይል ያሳየበት ቦታ  ማይካድራ ነው፤ 

👉የትህነግ ጥላቻ ከ1968 ማኔፌስቶውም በፊት ነው፤ ማንፌስቶው እኮ የአስተሳሰቡ ውጤት ነው፤ 

👉የትህነግ የማይካድራ ጭካኔና ጭፍጨፋ በፊት ከመጋረጃ ጀርባ እንደሚፈጸም በሀሜት ደረጃ ይሰማ የነበረው አሁን መጋረጃው የተገለጠበት ሰይጣንም          ያፈረበት ስራው  ነው፤ 

👉የጁንታው ውሸት አስገራሚ ነበር፤ እኔ ሁመራ ሆኜ ዘገባ እየሰራሁ፤ በሬዲዮ የሰማሁት የእነሱ ዜና ሁመራን ተቆጣጥረናል የሚል ነው፤ ደነገጥኩ የት ነው ያለሁት እኔ ነኝ ወይንስ ሁመራ ነው ወደሌላ ቦታ የሄደው እስክል ድረስ ተገረምኩ፤   

👉እነሱ ቢዋሹም አይናቸውና እጃቸው አይዋሽም ነበር፤ በሚዲያዎቻቸው እየቀረቡ ሲዋሹ ሁሉም ነገር ያስታውቅባቸው ነበር፤ 

👉የትህነግ ሀይል ገኖ ነበር የመጣው፤ በተለይ እኔ በነበርኩበት አብድራፊ በኩል አብድራፊን ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር፤ ሶሮቃን በዳንሻ በኩል ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር፤  በራያ በኩል ወደ ወልዲያ የመሄድ እቅድ ነበረው፤ 23ኛው ክፍለ ጦር ተበትኖ ስለነበረ ምንም አያስቀረውም ነበር። 

👉ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ዝግጁ ስለነበረና የኮንትሮባንድ ስራን ሲቆጣጠሩ በነበሩ ከተፈጸመባቸው ጥቃት ያመለጡ የፌዴራል ፖሊስ አባላትም ባደረጉት ተጋድሎና ጀግንነት ትህነግ ሊቆም ችሏል፤

👉ከፊት ለፊት በመሳሪያ ከጎናቸው በጓደኞቻቸው አስከሬን ሽታ ተፈትነው ድል ነስተዋል፤ ይሄንን ድል ያደረጉት በኢትዮጵያ ፍቅር ነው፤ በኢትዮጵጽያዊነት ነው፤ 

👉የአማራ ልዩ ሀይል ወደማይካድረ ከመሄዱ በፊት ሁለት የግዴታ አማራጮች ነበሩት፤ አንደኛው ያለውን ስንቅና ጥይት ለተበተኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እያጋራ መዝለቅ፤ የተማረከውን ሀይል ደግሞ ለመከላከያ እየሰጠ መሄድ ነበረበት፤ ይሄንን አደረገ፤  

👉ሁለተኛው አማራ ልዩ ኃይል ሌላኛው ጫና እነማይካድራን ማስለቀቅ፣ የሉግዲ መሿለኪያን ማስለቀቅ ወደ ሱዳን የሚሄደውን የትህነግ ኃይል የሚሾልከበትን በር መዝጋትና የሁመራን ቦታ መቆጣጠር  ብቻ ሳይሆን የተከበቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ከጓደኞቻቸው የአስክሬን ሽታ፣ ከተከበቡበትም ሕይወታቸውን ማትረፍ ግዴታው ነበረ፤ ሀላዊና በረከት ላይ ይህንን አደረገ፤

👉ወደ ማይካድራ ስንደርስ ደም ፈሷል፤ ሁሉም አዝኗል፤ ሁሉም ይተኩሳል፤ ከመኪና ስንወርድ ሁሉም በእኛ ተቆጥቷል፤ ምክንያቱም እኛ ድሉን ስናበስር ነው የቆየነው፤ 

👉እዛ ቦታ ላይ ደም ፈሷል፤ የራሳችንን ወገን ደም ረግጠናል፤ እዛ ቦታ ላይ በወደቀ የአስክሬን ብዛት መካከል መቆም ምናልባትም ትንፋሽን መቁጠር እስከሚያክል 
 ድረስ የምንተነፍሰው አየር ያስጨንቀን ነበር፤

👉በእንደዚህ አይነት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትንፋሽ ቅንጦት ነው፣ የልብ ምት ቅንጦት፤ ሁሉም ጭንቅላታቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም ሆዳቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም ደምተዋል፤ ሁሉም ወድቀዋል፤  አልጋ ያገኙት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ በእነዚህ መሃል መቆም በጣም ከባድ ነበር፤

👉በጋራ ሆነን ይህንን ነገር ለዓለም ማሳወቅ ነበረብን፤ ይህንን ዘግተነው ካለፍን አደገኛ ነበረ፤  መበርታት ነበረብን፣ ደም ረግጠን ነው የቆምነው፤  ሁላችንም ደም ረግጠናል፡፡ 

👉ይህንን ለቅሶ እዛ አላለቀስኩትም፣ ሰላም ስለሆነ ነው፤  ማልቀስም ሰላም በሆነበት ቦታ ነው የሚቻለው፣

👉ህዝብን አነጋገርን ወስደው እንደ ቀበሯቸው ነገሩን፤ ነገር ግን የተገደሉት እነዚህ ብቻ አይደሉም አሉን፤ 

👉ከቢሮ መቀሌ ትገባላችሁ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶናል፤ መቀሌ መግባት ለእኛ መዝናናት ነበር፤ ስለሆነም በየቦታው የተደፉ ሰዎችን ማሳየት ነበረብን፤ አሞራና ዝንብ እየተከተለን በየቦታው የወደቁ አስከሬኖችን አሳየን፤ 

👉 ዓለም የትህነግን መጥፎነት ያየው ያን ቀን ነበር፤ ምክንያቱም በፕሮፓጋንዳ ተሸፍኖ ነበረ፤  እኛ ገለጥነው፤ 

👉 ከአከባቢው ሰው ጋር ተባብረን በመጀመሪያው ቀን የ74 ሰዎችን አስከሬ አገኘን፤ 74ቱም ስዎች በጋራ ነው የተቀበሩት፤ የህጻናት ጫማ ነበረ፣ የሴቶች ነጠላ ነበረ፤

👉 አቡነ አረጋዊ በሚባለው ቦታ ላይ የተቀበሩት ሰዎች ቁጥራቸው አይታወቅም፤ በጣም የሚገርመው አስክሬኖቹን መቅበር የማይቻልበት ጊዜ ነው የተደረሰው፤ የአካባቢው ሰው የአስከሬኑን ሽታ ለመቋቋም ሲል ሽቶ ተጠቅመዋል፤ 

👉  ከሁለት ቀናት በኋላ ተመሳሳይ ጥቆማ ደረሰን፤ አሞራ አከባቢውን ይዞራል፤ ዝንቦች ወረውታል፤ 18 የደረቀ አስክሬን አንድ ላይ  ሳይቀበሩ አገኘን፤ እንዲሁ ነው የተደፉት፤ 

👉   እስከ መቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው አሁን ያለን አማራጭ  ኢትዮጵያ የሁላችንም ድምቀት መሆን አለባት፤ የሁላችንም ጌጥ ነው መሆን ያለባት፤  

👉  ኢትዮጵያን ተጭኖ የተለያዩ ብሔሮችን ዘር እየለየ የሚያጭድ የተንኮል ገበሬ ካለና እሱ ካልፀዳ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ መሆን አይችልም፤ 

👉  እያንዳንዱ ወታደር የተዋጋው በሸተተ ጓደኛው አስክሬ ጎን ሆኖ ነው፤  እዚህ ቦታ ላይ መቆም አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቻለሁ ከዚህ በፊት ልጄን ቀብሬያለው፤ አልከበደኝም፤ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ይሀንን መመስከር አይቻልም፤

👉 ሰው ካልሆንን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፤  እነዛ ሰዎች ሰውነታቸው ስለካዳቸው ነው ኢትዮጵያዊ መሆን ያልቻሉት፤

👉 ከዚህ በኋላ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የመጨረሻውን የተንኮል  ስለት የያዘው አካል በመከላከያ ሰራዊት፣ በልዩ ኃይል አባላት፣ በአፋር ልዩ ኃይል አባላት፣ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ደጀንነት ተሰናብቷል፤

“It can be very easy to see a corpse;  I see them too.  I have already buried my one-year-old son;  It didn't bother me.  But it is not possible to stop at Maikadra;  It is impossible to testify to everything I have seen,  The feeling is very intense.  If w I resist and report it,  If we had not stopped, the crime would have been hidden. ”- Journalist Wondar Mekonnen
 ***************************
 (EPD)

 The Ethiopian Press Agency is celebrating its 80th anniversary in various forums throughout the year.  As part of the celebration, he held a thanksgiving and discussion forum for media professionals involved in the law enforcement campaign.

 Amhara journalist Wondat Mekonnen, who witnessed the massacre of one of the leading journalists on the program, shared his thoughts with the audience.

 It can be very easy to see a corpse;  I saw them too.  I have already buried my one-year-old son;  It didn't bother me.  But it is not possible to stop at Maikadra;  It is impossible to testify to everything they have seen,  The feeling is very intense.  If we had not reported it and stopped it, the crime would have been hidden, ”said Wondar.

 What I have seen is painful,  If these diseases had not stopped us, Ethiopia would not have remained Ethiopia;  To be honest, Ethiopia would not be Ethiopia if the people of Kaddara could not bear the pain.

 Here are some of the key issues raised by journalist Wondatur during his eyewitness speech:

 ተውThe ones who died in Maikadra were mainly Amhara but Oromo also died;  Wolayita is dead,  Somalia is dead;

 ቦታ It is a place where the TPLF has shown that it will not back down from the sharp point of the sword.

 👉The hatred of the TPLF was before the 1968 Manifesto;  The manifesto is the result of his thinking;

 👉 He was rumored to be behind the curtain before the TPLF's unspeakable brutality and massacre.

 👉Junta's lie was amazing;  I am Humera, reporting;  I heard on the radio that they had taken control of Humera.  I was shocked and wondered if it was me or Humera who had gone somewhere else.

 ቢ Although they lied, their eyes and hands did not lie;  When he lied to them in the media, he told them everything;

 👉 He came from the power of the law;  In particular, through Abdrafi, where I was, he took control of Abdrafi to Gondar;  Sorokan took control of Gondar via Dansha,  He planned to go to Woldia through Raya;  The 23rd Battalion was dispersed, and nothing was left of it.

 ስለBut, because the Amhara Regional State Special Forces was ready and the Federal Police members who escaped the attack while controlling the smuggling operation, the struggle was stopped by the TPLF.

 👉 In front of them, they were tested by the smell of the corpses of their friends.  They have achieved this with the love of Ethiopia;  It is Ethiopian;

 በፊትAmhara Special Forces had two mandatory options before moving to Maikader;  One is to share the ammunition and ammunition with the scattered members of the Defense Forces;  He had to give his captives power;  He did this:

 ሌላ The second pressure of the Second Amhara Special Forces was to liberate Enaykadran, to liberate the Lugdi tunnel, not only to close the TNG entrance to Sudan and to take control of Humera, but also to protect the members of the Defense Forces from the smell of their comrades' corpses.  He did this in the presence of blessings and blessings;

 ስን When we reached Maikadra, there was bloodshed;  Everyone is sad,  Everyone shoots;  When we got out of the car, everyone was angry with us;  Because we have been announcing the victory;

 ደም There was bloodshed there;  We have trampled on our own blood;  Standing in the middle of a large number of corpses lying there, perhaps to the point of counting your breath
 We were worried about the air we were breathing,

 ትን In such a dangerous situation, breathing is a luxury, a heartbeat is a luxury;  All their heads are open,  They all have their stomachs open,  They all bleed;  They have all fallen,  Very few have found a bed.  It was very difficult to stand in the middle of them,

 ብን Together we should have made this known to the world;  It would have been dangerous if we had closed this;  We had to be strong, we stood on blood;  We are all covered in blood.

 አ I did not cry this cry because it is peace;  Crying is possible only in a place of peace,

 👉 They took the public speech and told us that they were buried;  But they are not the only ones who were killed.

 ናል We have been instructed to enter the office.  Entering Mekele was fun for us;  So we had to show people everywhere;  The vultures and flies followed us and showed us the corpses that had fallen everywhere;

 ነበር That was the day the world saw the evil of the law;  Because it was covered with propaganda;  We revealed it:

 በመጀመሪያው Together with a local man, we found the bodies of 74 people on the first day;  All 74 were buried together;  There were children's shoes, women's socks;

 ሰዎች The number of people buried in Abune Aregawi is unknown;  Surprisingly, the time came when the corpses could not be buried;  The local people used perfume to resist the smell of the corpse;

 👉 Two days later, we received the same report:  The eagle walks around;  Flies infest it;  18 We found a dead body without a burial place;  That's how they fell:

 መቼ How long will we continue in this situation? Our current option should be the highlight of all of us.  It should be the ornament of all of us;

 ካለ Ethiopianness cannot be Ethiopia if there is a malicious farmer who oppresses Ethiopians and divides the races of different nations.

 👉 Each soldier fought alongside the body of his sick friend;  Standing here can be very easy to see a corpse;  I have seen that I have buried my son before,  It is not hard for me;  But it is not possible to stop at Maikadra;  This cannot be proved;
 It is impossible to be Ethiopian if we are not human;  Those people could not be Ethiopians because their bodies denied it;

  After this, the person who took the last sharp edge in this situation was dismissed by the Defense Forces, members of the Special Forces, members of the Afar Special Forces, and all Ethiopians.

 

No comments:

Post a Comment