ሰቆጣ፤ ህዳር 30/2013 (ኢዜአ) ''የህወሃት ጁንታው ቡድን ማንነትን መሰረት በማድረግ ብቻ በእስር ቤት ውስጥ በሰለጠኑ ውሾች እስከማስነከስ ግፍ ፈጽሞብናል ሲሉ በኮረም ከተማ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ገለጹ።
መንግስት በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ጁንታው ከተወገደ ወዲህ የኮረም ከተማ ወደቀደመ አንጻራዊ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ እክያው ተመስገን እንደገለጹት የህወሃት የጥፋት ቡድን የሰው ልጅ ይፈፅመዋል የማይባለውን በደል ሲፈፅም ቆይቷል።
ቡድኑ ባለፉት 30 ዓመታት የኮረም ከተማ ነዋሪዎች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸው የታፈነበት አስቸጋሪ ወቅት እንደነበረም ጠቅሰዋል።
"ማንነታችንን መሰረት በማድረግ ብቻ ድብደባና እስር ይደርስብን ነበር" ያሉት አቶ እክያው በፖሊስ ጣቢያ ታስረው በሰለጠኑ ውሾች ያስነክሷቸው እንደነበር አስታውሰዋል።
ሌሎች ከሃምሳ በላይ ሰዎችም በውሻ እንዲነከሱ ተደርገው ተመሳሳይ ግፍ እንደተፈጸመባቸው አመልክተዋል።
''በእኔ ላይ የሚደርሰውን ተደጋጋሚ ግፍና በደል መቋቋም ያልቻሉ ልጆቼ ከተማውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ኑሯቸውን እንዲገፉ ተገደዋል'' ሲሉም ተናግረዋል።
ቡድኑ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን የክህደት ጥቃት ተከትሎ መንግስት በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ኮረም ከተማ ከጁንታው አገዛዝ ነጻ በመውጣት ወደ ቀደመ አንጻራዊ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑንም ገልጸዋል።
"ባለፉት 30 አመት የኦፍላ ወረዳና የኮረም ከተማ ነዋሪዎች ማንነትን መሰረት በማድረግ በሚፈጸም ግፍና በደል ተሳቀው ቀያቸውን ለቀው ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በመሄድ እንዲኖሩ ተገደዋል" ያሉት ደግሞ የከተማው ነዋሪ አቶ ሃይሉ ተስፋዬ ናቸው።
ቡድኑ በገዛባቸው አመታት በኮረም ከተማ በመሰረተ ልማት አገልግልት ተጠቃሚ እንዳልነበረች የገለጹት አቶ ሀይሉ፤ በአካባቢው ለችቡድ ፋብሪካ ማምረቻ በቂ ግብዓት እያለ ፋብሪካው ሌላ አካባቢ እንዲቋቋም እሰከ ማድረግ ከስከፊ ተግባር መፈጸሙን ጠቅሰዋል።
"የከተማው ወጣትም የስራ እድል ሳይፈጠርለት ቆይቷል" ያሉት አቶ ሀይሉ አሁን በመጣው ለውጥ ትልቁ ተቋዳሽ ወጣቱ እንደሚሆን አመላክተዋል።
"የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሃይል ጁንታው ላይ በወሰዱት ህግ የማስከበር እርምጃ ለኦፍላ ወረዳና ለኮረም ከተማ ነዋሪዎች ትልቅ ተስፋን ፈንጥቋል" ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን ላይ አካባቢው ወደ ቀደመው ሰላሙ መመለሱን አመልክተዋል።
ወጣት በርሄ ማርየ በበኩሉ ህወሃትን የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ድጋፍ አድርገሃል በሚል ለስድስት አመታት በማረሚያ ቤት ታስሮ በደል እንደደረሰበት ተናግሯል፡፡
"ከእስር ከወጣሁ በኋላም ወንጀል ፈጽመሀል በሚል የስራ ፈጠራ የገንዘብ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆን ተደርጊያለሁ" ብሏል።
አሁን ላይ በመጣው ለውጥ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ ለውጡ ለወጣቶች ሰርቶ ለመለወጥ ትልቅ አስተዋጾ እንዳለው ወጣት በርሄ ገልጿል።
≠
Junta has abused us to the point of biting us in prison by trained dogs ... Amhara natives in Korem town
Sekota: November 30, 2013 (ENA) - Amhara residents in Korem town say that the TPLF Junta group has abused us by biting dogs in prison on the basis of their identities.
The reward of his reward.
Residents told ENA that Korem town has been returning to its former relative peace since the removal of the junta following the government's crackdown.
A resident of the town, Ekew Temesgen, said the TPLF has been committing atrocities against humanity.
The group also noted that Korem has been a difficult time for the past 30 years.
"We were beaten and arrested just because of who we were," he said, recalling that they had been detained at the police station and bitten by trained dogs.
More than 50 other people reported that they had been bitten by dogs.
"My children, who could not cope with the repeated abuse, were forced to leave the city and move to Addis Ababa to make a living," he said.
He said Korem was liberated from the junta and returned to normalcy following the government's crackdown on the army.
"For the past 30 years, residents of Ofla woreda and Korem town have been forced to leave their villages and live in other parts of the country, laughing at identity-based violence," said Hailu Tesfaye, a resident of the town.
Hailu said the group did not benefit from infrastructure services in Korem during its years. He said that while there is enough inputs for the production of Chubud Factory in the area, it is a bad thing that the factory was set up in another area.
"The city's youth have not been given job opportunities," Hailu said, adding that he will be the biggest beneficiary of the current changes.
"The law enforcement action taken by the Defense Forces and the Amhara Special Forces in Junta has given great hope to the residents of Ofla Woreda and Korem town," he said.
He said the area is now back to normal.
Young Berhe Marie, for his part, said he had been imprisoned and abused for six years for allegedly supporting anti-TPLF political parties.
"Even after my release, I was denied access to a job creation loan," he said.
Berhe said he is happy with the change and said that the change will help young people to change.
No comments:
Post a Comment