አማርኛ ቋንቋን በመጠቀም ጭምር ያልተነገሩ ነባር የአፍሪካ ታሪኮችን ወደ ድምፅ መጽሐፍት መቀየር የሚያስችል መተግበሪያ ተሠራ-ሲ.ኤን.ኤን
*******************************
የአፍሪካውያን ያልተነገሩ ነባር ታሪኮችን ወደ ድምፅ መጽሐፍት በመቀየር ወጣቱ ትውልድ ስለ ባሕሉ እና ታሪኩ እንዲያውቅ ለማድረግ በመዝናኛ እና በትምህርት መልኩ ማቅረብ የሚያስችል መተግበሪያ ተሠራ።
የጋናው ግዙፍ የሶፍት ዌር ኩባንያ ሶፍትትራይብ ባለቤት ሄርማን ቺነሪይ-ሄስ አፍሪካውያን አፈ ታሪኮችን በአዲሱ የድምፅ መጽሐፍ መተግበሪያ ለትውልድ ለማስተላለፍ መነሣቱን ተናግሯል።
ይኸው የአፍሪካውያን ድምፆች (Afrikan Echoes) የተሰኘው መተግበሪያ በመጪው መጋቢት ወር ውስጥ እስካሁን ያልተነገሩ 50 የአፍሪካውያን ነባር ታሪኮችን በዩሩባ፣ አማርኛ እና ስዋሂሊ ቋንቋዎችን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎች ተርጉሞ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
የመተግበሪያው ባለቤት የተዘጋጀው የመተገበሪያ ሥርዓት (ፕላትፎርም) በየትኛውም አኗኗር ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ያልተነገሩ ታሪኮቻቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ማድረስ እንደሚያስችላቸው ገልጿል።
በመላው አህጉሪቱ የሚኖሩ አፍሪካውያን የታሪክ ተናጋሪዎች ታሪካቸውን በራሳቸው ቋንቋ በድምፅ በመቅረጽ ለአፍሪካውያን ድምፆች (Afrikan Echoes) መላክ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል።
የተላኩ ድምፆች ወደ ስቱዲዮ ገብተው ወደ መተግበሪያው እንዲካተቱ ከመደረጋቸው አስቀድሞ በሶፍትትራይብ ኩባንያው ባለቤት ሄርማን ቺነሪይ-ሄስ አማካኝነት በተቋቋመው የፈጠራ ባለሞያዎች ቡድን እንደሚገመገሙ ተገልጿል።
“አሁን ባለንበት ዓለም ነባር ዕውቀቶች በኤሌክትሮኒክ ድምፅ አማካኝነት መተላለፍ ይችላሉ” ያለው ሄርማን ቺነሪይ-ሄስ “በመሆኑም እኛ አፍሪካውያን ነባር ዕውቀቶቻችንን ስልኮቻችን ላይ ለማግኘት እየጣርን ነው” በማለት ለሲኤንኤን ተናግሯል።
አያይዞም፣ “አፍሪካውያን ያልሆኑ ሰዎች የአፍሪካውያንን ታሪኮች በአፍሪካውያን እና በአፍሪካውያን የአነጋገር ዘዬ ሲነገሩ ለማዳመጥ ያስችላቸዋል” ብሏል።
App uses Amharic language to translate previously unspoken African stories into audio books: CNN
***********************************
An application was made to entertain and educate the younger generation about the culture and history by translating untold African stories into audio books.
Herman Chinnery-Hes, owner of software giant Ghana, said it has set out to pass on African legends to its new audiobook application.
The Afrikan Echoes app is expected to translate 50 African stories in several African languages, including Yoruba, Amharic and Swahili, in March.
The owner of the app says that the platform will enable people of all walks of life to share their unspoken stories on a global platform.
He also suggested that African historians across the continent record their stories in their own language and send them to Afrikan Echoes.
The audio will be reviewed by a team of innovators set up by software company Herman Chineri-Hess before it can be added to the studio and integrated into the app.
"In today's world, existing knowledge can be transmitted electronically," said Herman Chineri-Hess.
No comments:
Post a Comment