Shop Amazon

Sunday, January 24, 2021

Ethiopian Land Tenure and Property Rights Law

የኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ እና የቤት ባለቤትነት መብት ህግ

የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብቶች የንብረት መብቶች ሲሆኑ ከማይነቀሳቀሱ የንብረት መብቶች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው (የፍ/ህ/ቁ 1030)፡፡ ይህም ሁለቱን መብቶች አንድ የሚያደርጋቸው የመጀመርያው ጉዳይ ነው፡፡ 

 ዜጎች በመሬት ላይ ያላቸው መብት  የመሬት ይዞታ መብት ሲሆን ከሽያጭ በስተቀር በመሬቱ ላይ የመጠቀም፣ የይዞታ መብታቸውን በስጦታ፣ በውርስና በኪራይ ለማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ 

በሌላ በኩል የግል የቤት ባለቤትነት መብት ደግሞ ለሁሉም ዜጎች እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶች በእኩልነት የተሰጠ መብት ሲሆን የቤት ባለንብረት የሆኑ ግለሰቦች ወይም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በቤቱ ላይ የመጠቀም፣ በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የመሸጥ እና በሌላ ማንኛውም መንገድ ንብረቱን ለሌላ ወገን  የማስተላለፍ መብት የሚሰጥ ነው፡፡

የቤት የግል ንብረት ባለቤትነት ባለቤቱ ቤቱን በሽያጭ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች የንብረት መብቶችን የሚሰጥ ሰፊ መብት ነው፡፡ እዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ አንድ የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ሁለት መብቶችን አጣምሮ የያዘ ስለመሆኑ ነው፡፡ የመጀመርያው ቤቱን የገነባበት የመሬት ይዞታ መብቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመሬቱ ላይ የተገነባው ቤት ባለቤትነት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁለት የንብረት መብቶች ለየብቻ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባይሆንም የመሬቱ ባለቤት መንግስት እና ህዝብ ሲሆን የቤቱ ባለቤት ደግሞ ቤቱን የገነባው የመሬት ባለይዞታ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡  ስለሆነም አንድ የቤት ባለቤት በይዞታ መሬቱ ላይ ቤት ሰርቶ ሲሸጥ ቤቱ እና ቤቱ የተሰራበት ይዞታ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባለመሆናቸው (intrinsic element) በመሆናቸው የይዞታ መብቱንም ጭምር በሽያጭ እንዳስተላለፈ ይቆጣራል፡፡ 

የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ብሄረሰቦች (አርሶ አደሮች፣ ዘላኖች እና የከተማ ኗሪዎች) በእኩልነት የመሬት ባለቤቶች እንደሆኑ ህገመንግስቱ በማያሻማ ሁኔታ ደንግጓል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ዜጋ እኩል የሆነ የመሬት ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ ተረጋግጧል ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የመሬት ስሪት በገጠር እና በከተማ በልዩነት ሊታይ የሚችል አይደለም፡፡ በገጠር እና በከተማ የመሬት ስሪት ልዩነት አለው ከተባለም ልዩነቱ መምጣት ያለበት አርሶ አደሩ ወይም ዘላኑ የገጠር የእርሻ መሬትና የግጦሽ መሬት ፍላጎት ያለው መሆኑ ሲሆን የከተማው ነዋሪ ደግሞ የመኖርያ ቤት መስርያ ወይም ለተሰማረበት የንግድ ስራ የሚመጥን የድርጅት ቤት መገንቢያ መሬት የማግኘት ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ብቻ ነው፡፡

ስለሆነም ከፍ ሲል እንደገለጽነው ህገመንግስቱ በመርህ ደረጃ መሬት የህዝብ እና የመንግስት ነው ካለ በገጠር ያለውን የእርሻ መሬት እና የግጦሽ መሬት ለአርሶ አደሩ እና ለዘላኑ በነጻ እንዲተላለፍ ከፈቀደ በከተማ ለሚኖረው ነዋሪ እና ነጋዴም የቤት መስርያ ቦታ እና ለንግድ ድርጅቱ የሚያስፈልገውን የመስርያ ቦታ በነጻ ወይም ያለክፍያ ሊያገኝ ይገባው ነበር፡፡ 

እዚህ ላይ በአትኩሮት ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ በአሁኑ ስዓት በሃገራችን በተለይም በከተሞች አካባቢ የኗሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አዳዲስ ከተሞች ሳይቀር እየተፈጠሩ የመጡበት ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የመኖርያ ቤት እጥረት አለ፡፡ ይህንን ችግር በመገንዘብ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና የከተማ የመሬት ስሪት አዋጆችን በማውጣት ወደስራ ገብቶ የነበር ቢሆነም የመኖርያ ቤት ችግሩን ለመቅረፍ አልቻለም፡፡ መጠለያ የማግኘት መብት ደግሞ መሰረታዊ መብት በመሆኑ በማንኛውም ምክንያት ሊገደብ የሚችል አይደለም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ በሃገሪቱ ሁሉም ክልሎች ተዘዋውሮ የመስራት እና በሚሰራበት አካባቢ የመኖርያ ቤት መስርሪያ ቦታ የማግኘት መብቱ ሊከበርለት ይገባ ነበር፡፡

ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የገጠር ኗሪው አርሶ አደር ወይም ዘላን መሬትን በነጻ የማግኘት እና በዚሁ መሬቱ ላይ የመኖርያ ቤት የመገንባት እና የቤት ባለቤት የመሆን እንዲሁም በመሬቱ ላይ የግብርና ስራዎችን የማከናወን ኢኮነሚያዊ መብቱ የተረጋገጠለት ሲሆን የከተማው ነዋሪ በተቃራኒው ግን መሬትን ለመኖርያ ቤት መስርያም ይሁን ለንግድ ስራው ማካሄጃ የሚያገኘው በክፍያ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ የገጠሩ ኗሪ መሬትን በነጻ የሚያገኘው ቢሆነም ከዚህ ይዞታው ሲነሳም መንግስት ወይም የከተማው ነዋሪ ተገቢው ካሳ የሚከፈለው መሆኑ ሲሆን በመሬቱ ላይ እኩል መብት ያለው የከተማው ነዋሪ በገጠር ለሚኖርው ካሳ እንዲከፍል መደረጉ የፍትሃዊነት ጥያቄን ከማስነሳቱ ባሻገር በከተማ የሚኖሩ ዜጎችን በሃገሪቱ ኢኮነሚ እኩል ተጠቃሚ የመሆንን እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን የሚገድብ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ያለው የገጠር መሬትን ለማስተዳደር የወጡ አዋጆች በከተማ ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም የከተማ ነዋሪ ስራውን ትቶ አርሶ አደር ስካልሆነ ድረስ የገጠር መሬት ተጠቃሚ መሆን እንደማይችል የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒ በገጠር የመኖርያ ቤት ሰርቶ የቤት ባለቤት የሆነው እና በእርሻ ስራ የሚተዳደረው አርሶ አደር ግን እንደከተማው ኗሪ በከተማ የመኖርያም ይሁን የንግድ ድርጅት መስርያ ቦታን በህግ በተወሰነ ክፍያ በእኩልነት የማግኘት መብቱ ተረጋገጠ ነው።

Ethiopian Land Tenure and Property Rights Act

 Land rights and property rights are property rights and are classified as immovable property rights (Law 1030).  This is the first thing that unites the two rights.

 Citizens' right to land is the right to own land, which can be used for sale, inheritance, inheritance and lease, except for sale.

 Private property ownership, on the other hand, is an equal right for all citizens and legal entities, and gives homeowners or legal entities the right to use, gift or inherit the home, sell it, and transfer the property in any other way.

 Private property ownership is a broad right that gives the owner other property rights, including the sale of the home.  The point is, a homeowner has two rights.  The first is the right to own the land on which the house is built, and the second is the right to own the house built on the land.  Although these two property rights cannot be viewed separately, the landowner is the government and the people, and the landlord is the person or organization that built the house.  Therefore, when a landlord builds a house on the land and sells it, the house and the house are not considered separate (intrinsic element).

No comments:

Post a Comment