Shop Amazon

Wednesday, February 3, 2021

በኢትዮጵያ ሳምሪ በተሰኙ የጁንታው ኃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋ የሽብር ወንጀል ነው-ኢንተርፖል

በኢትዮጵያ ሳምሪ በተሰኙ የጁንታው ኃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋ የሽብር ወንጀል ነው-ኢንተርፖል
*************************
ጁንታው ባሰማራቸው ሳምሪ በተሰኙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮ ሃራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈጸመው የሽብር ወንጀል በመቅደም በርካታ ንጹሐን ዜጎች የተገደሉበት ወንጀል ሆኖ መመዝገቡን ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም (ኢንተርፖል) አስታወቀ።

እ.አ.አ ኅዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈጸሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በጁንታው ፀረ ሰላም ኃይሎች ማይካድራ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ቦኮ ሃራም እና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለያዩ ሀገራት ከፈጸሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንጹሐን ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ነው። 

ጁንታው እኩይ ተልእኮውን ለማሳካት አስታጥቆ ያሰማራቸው ሳምሪ የተሰኙ የሰላም ተፃራሪ ኃይሎች በማይካድራ በፈጸሙት ማንነትን መሠረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።

ከሦስት ወራት በፊት በኅዳር ወር ላይ ብቻ በተፈጸሙ የሽብር ወንጀሎች አፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ መቀመጧን የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ንጹሐን ላይ ባነጣጠሩ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በርካታ ሕይወት መቀጠፉን አስገንዝቧል።
 
የሽብር ቡድኖቹ ከሰብአዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸውን የጅምላ ጭፍጨፋዎች መፈጻማቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከአፍሪካ በመቀጠል ደቡባዊ የእስያ አካባቢ እና ምሥራቃዊ የሜዲትራኒያን ቀጠና የዚህ ሽብር ወንጀል ሰለባ መሆናቸው ተጠቁሟል።

እ.አ.አ ኅዳር 2020 ኅዳር ወር ላይ ብቻ በተፈጸሙ እና በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸውን ባጡባቸው የሽብር ወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኢንተርፖል መረጃ በኢትዮጵያ ማይካድራ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ እና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮ ሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብአዊነት ላይ ከተፈጸሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ መሰለፋቸውን ያሳያል ተብሏል። 

የተለያዩ ኢ-ሰብአዊ ዓላማዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በንጹሐን ላይ የሚፈጽሟቸው ግድያዎች አሳሳቢ መሆናቸውም በመረጃው ላይ ተጠቅሷል።

ከሦስት ወራት በፊት የንጹሐንን ሕይወት የቀጠፉ የሽብር ወንጀሎች ከተፈጸሙባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ሞዛምቢክን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ሶማሊያን፣ ቡርኪናፋሶንና ቻድን የያዘችው አፍሪካ በግንባር ቀደምትነት የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ደግሞ ከደቡብ እስያ አፍጋኒስታን፣ ከምሥራቅ ሜዲትራኒያን ሶሪያን እንዲሁም ኢንዶኔዥያን እና ኦስትሪያን አካትቷል። የሽብር ቡድኖቹ በእነዚህ ሀገራት በፈጸሟቸው አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎች እ.ኤ.አ በኅዳር ወር 2020 ዓ.ም ብቻ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።

ኢንተርፖል ያሰባሰበው የመረጃው ግኝት እንደሚያሳየው መንግሥታዊ ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ከተፈጸሙ ጥቃቶች አራቱ እና በከፍተኛ ሁኔታ የንፁሐንን ሕይወት የቀጠፉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ (በዋናነት በአፍጋኒስታን) በባሕረ ሰላጤ አካባቢ ሀገራት በዋነኝነት በየመን እና በምሥራቅ ሜዲትራኒያን (በሶሪያ) የተፈጸሙ መሆናቸውንም ያመላከተ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሳምሪ የተሰኙ የጁንታው ኃይሎች ማይካድራ ላይ እንዲሁም በናይጄሪያ ቦኮ ሃራም የፈጸሙት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ከሁሉም የከፋ እልቂት የተመዘገበባቸው የሽብር ወንጀሎች መሆናቸውን ገልጿል።
Massacre in Maikadra of Ethiopian Samaritan forces, Samri: Terrorism: Interpol
 ***************************

 The Boko Haram massacre in Makadra by anti-peace forces deployed by Junta was preceded by a terrorist attack in Nigeria earlier this month, killing scores of innocent people, according to the International Police Organization (Interpol).

 According to Interpol, the report on the 10 worst terrorist attacks in the world in November 2020 shows that the massacre in Boko Haram by Boko Haram and other terrorist groups is more than the number of innocent people killed in various countries.  It is an inhumane act in which people lose their lives.

 According to the Interpol's Counter-Crime Prevention Directorate, 600 innocent civilians were killed in a suicide bombing carried out by the anti-peace group Samri, which was deployed by Junta to carry out its mission.

 According to Interpol, three months ago, Africa was at the forefront of terrorist attacks in November alone, killing scores of innocent people.

 Terrorist groups are said to have carried out unprovoked massacres of human beings, followed by South Asia and the eastern Mediterranean region.

 Interpol's focus on the terrorist attacks that took place in November 2020 alone, in which scores of people were tragically killed, are the latest in a string of atrocities committed by the Boko Haram massacre in Maikadura, Ethiopia, and the Boko Haram massacre in Nigeria.  It is said that they are in line.

 The report also said that the killings of innocent people by terrorist groups with various inhumane motives are also a concern.

 Interpol reports that Africa, which included Ethiopia, Nigeria, Mozambique, the Democratic Republic of the Congo, Somalia, Burkina Faso and Chad, were among the countries where terrorist attacks took place three months ago.  According to Interpol, in November 2020 alone, nearly 1,000 innocent people were killed by terrorist groups in these countries.

 The data collected by Interpol shows that four of the most serious terrorist attacks in non-governmental groups have been committed in Africa, South Asia (mainly Afghanistan), Gulf states, mainly Yemen and the Eastern Mediterranean (Syria), Ethiopia, and Syria.  He described the massacres in Maiduguri and Boko Haram in Nigeria as one of the worst in the world.


No comments:

Post a Comment