ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያደርሱ ጥሪ አቀረቡ
*********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያደርሱ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልእክት የሚከተለው ነው፡-
የእናት ሆድ ዥንጉርጉርነት የልጆችዋን መልክና ጠባይ አንድ አይነት እንደማያደርገው ሁሉ፤ ከኢትዮጵያ ማህጸን በቅለው፣ የክብር ቦታ አግኝተውና ከሩብ ክፍለ ዘመን ለተሻገረ ጊዜ ሀገር የአስተዳደሩ ሰዎች መልሰው ሀገራችንን ከጀርባ ቢወጓት፥ የእናትን ውርደት በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ርብርብ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ዳሩ ግን፥ ዛሬም የጁንታው ሞት ያልተዋጠላቸው ከዥንጉርጉር ማህጸኗ የፈለቁ ሰዎች ከሀገራችን ጠላቶች ጋር እያበሩ፣ የተዛቡ መረጃዎች መርጨቱን የዕለት እንጀራቸው አድርገውታል። እንዳሻቸው መሆን ካልቻሉ ኢትዮጵያ እንድትኖር አይፈልጉም። በሕግ ማስከበር ዘመቻው ያጡትን ድል በወሬ ግንባር ለመመለስ ተንኮልን መሣሪያ፣ ሐሰትን ጥይት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
በመሆኑም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፥ ስለ ሀገራችሁና ስለ ወቅታዊው ጉዳይ ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በመናገር፤ የሀገራችንን መልካም ክብርና ስም ለማጥፋት የተነሱ ሰዎችን ድል በመንሳት፤ ሐሰትን በእውነት እንድታሸንፉ ጥሪ አቀርባለሁ።
Prime Minister Abiy Ahmed called on Ethiopians and friends around the world to provide accurate information to the international community
*********************
Prime Minister Abiy Ahmed called on Ethiopians and friends of Ethiopia around the world to provide accurate information on current national issues to the international community.
The Prime Minister's message on his social media page is as follows:
Just as a mother's womb does not have the same shape and behavior as her babies, If the people of the country who came from the womb of Ethiopia, gained a place of honor and fought back for a quarter of a century and pushed our country backwards, they will be dealt with by the efforts of Ethiopians who do not want to humiliate their mother.
However, even today, those who did not accept the death of Junta were shining with the enemies of our country, making the spread of misinformation their daily bread. If they can't be what they want to be, they don't want Ethiopia to exist. They continue to use deceptive weapons and false bullets to retaliate.
Therefore, Ethiopians and friends of Ethiopia around the world, by providing accurate information about your country and current affairs to the international community; By defeating those who seek to tarnish the image and reputation of our country; I urge you to overcome falsehood.
No comments:
Post a Comment