Shop Amazon

Wednesday, February 17, 2021

One of the signs of the TPLF's lack of modern warfare skills is the way it started the war.( President Isaias Afewerki)

ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ከተናገሩት መካከል
.
-  ህወሓት የዘመናዊ ውጊያ ጥበብና ብቃት እንደሌለው  ከሚያሳዩ ነገሮች አንዱ ጦርነቱን የጀመረበት መንገድ ነው::

-  ህወሓት በእንደዚህ አይነት ድፍረት ውጊያ ይጀምራል ብለን በፍፁም አልገመትንም::

- ያለ ምንም ምክንያት በኤርትራ ላይ ሮኬት መተኮሱ በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰራዊት መካከል ግጭት እንዲፈጠር እና በዚህ ግርግር መሐል ጥፋት ለመፈፀም ነው::  

-  ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያና ኤርትራን እርቅና  ወንድማማችነትን ወደ ነበረበት ለመመለስ አዲስ ግንኙነት ስንጀምር ከደብረፂዮን ጋር እንድወያይ  ዶክተር አብይ ጠይቆኝ ነበር፣ እኔ ግን በፍፁም ፈቃደኛ አልነበርኩም:: ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በስልጣን ላይ በነበሩበት 20 አመታት በኤርትራ ላይ የነበራቸው ፖሊሲ የውይይት ሳይሆን የጥፋትና የእብሪት አቋም ነበር::  አሁን በህዝብ ትግል ሲባረሩ እንወያይ ማለት ራሳቸውን ማታለላቸው ነው::

- ከአመት በፊት በኦማሓጀር በኩል የኢትዮጵያና ኤርትራን ድንበር መከፈት ከዶክተር አብይ ጋር በቦታው በተገኘንበት ወቅት ደብረፂዮን ስነስርአቱ ላይ ነበር:: በአጋጣሚው ሊያናግረኝም ፈልጎ ነበር::  እኔ ግን አንድ ነገር ብዬው ነው የተለያየነው::  
"ህወሓት የኢትዮጵያና ኤርትራን አዲስ ወዳጅነትና ትብብር ለማደናቀፍ እየሞከረ እንደሆነ በጥብቅ የደህንነት ክትትል እያደረግንበት ነው።  መጀመርያ ወደ ሰላም ተመለሱ ሴራ እና የሽብር አስተሳሰብና ተግባር አቁሙ እና ወደ ትብብር መንፈስ እንመጣለን። ከዛ ውጪ እንደ አንድ ፓርቲና የክልል መንግስት ከናንተ ጋር የምንፈጥረው ግንኙነት አይኖርም ነው" ያልኩት::

- የኢትዮጵያና ኤርትራን ህዝብ አንድነትና ትስስር ልበጥስ ብትልም አትችልም። ይሄንን ደግሞ ወያኔ ለ25 አመታት ከሰራው ተግባር በሗላ አሁን ዳግም ፍቅር መፈጠሩና በኤርትራ ከተሞች ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ኤርትራውያን በናፍቆት ሲመላለሱ ማየት በቂ ምስክር ነው።
ይቀጥላል ...

@የተፌ ማስታወሻ
 President Isaias Afewerki
 .
 - One of the signs of the TPLF's lack of modern warfare skills is the way it started the war.

 - We never imagined that the TPLF would start a war with such boldness.

 - Rocket fire in Eritrea for no apparent reason is intended to provoke conflict between the Ethiopian and Eritrean forces and to destabilize the country.

 In the past, Dr. Abiy asked me to talk to Debretsion when we started a new relationship to restore Ethiopian-Eritrean reconciliation, but I refused.  Because the policy of these people in Eritrea during their 20 years in power was not a matter of dialogue, it was a matter of aggression and arrogance.  Now that they have been expelled by the people's struggle, let's talk.

 - A year ago, the opening of the Ethiopian-Eritrean border through Omahager was at Debretsion when we were there with Dr. Abiy.  Coincidentally, he wanted to talk to me.  But I have one thing in common.
 "We are keeping a close eye on whether the TPLF is trying to undermine the new friendship and cooperation between Ethiopia and Eritrea.

 - You can't break the unity and solidarity of the people of Ethiopia and Eritrea.  This is a testament to the resurgence of love after 25 years of TPLF activity and the longing for Ethiopians in Eritrean cities and Eritreans in Ethiopian cities.
 to be continued ...

 @ Tefe Note

No comments:

Post a Comment