ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ መኪና ተበረከተ
******************
የሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በተወረረበት ወቅት ለሕዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ መኪና ተበረከተላቸው።
የተሽከርካሪ ስጦታውን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አስረክበዋቸዋል።
የብጹዕነታቸውን ተሽከርካሪ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንደዘረፋቸው ይታወቃል።
ዛሬ በስጦታ የተረከቡት ተሽከርካሪም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል።
አቡነ ኤርሚያስም መንግሥት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
A car was donated to Blessed Abune Ermias
******************
When the North Wollo Zone was invaded by the terrorist group TPLF, they were given a car belonging to Abune Ermias, a true father of the people.
The donation was handed over by Minister of Revenue, Lake Ayalew, Minister of Transport and Logistics Dagmawit Moges, State Minister of Finance, Job Tekalign, and Customs Commissioner, Debele Kabeta.
They are known to have been robbed of their vehicle by the TPLF terrorist group.
It is also stated that the donated vehicles will cost over 6 million birr.
Abune Ermias also thanked the government for its support, ENA reported.

No comments:
Post a Comment