"ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው" በሚል መሪ ቃል በሳንድያጎ ከተማ ለወገኖቻችን እርዳታ በተሰበሰብው ገንዘብ የእህል እርዳታ ይዞ የሄደው የልዑካን ቡድን ሰመራ ከተማ አፋር ክልል ደረሰ።
የልኡካን ቡድኑ አባላት ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ፣ አቶ አቶ ስዮም ደገፋ እና ወ/ሮ እመቤት እንግዳው |
(YebboMedia Jan 10,2022 ጥር ፪፣2ሺ፲፬) "ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው" በሚል መሪ ቃል በሳንድያጎ ከተማ ለወገኖቻችን እርዳታ እንዲደርስ ከተደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ከተዋጣው $195000 ዶላር ላይ 60% የሚሆነው በባንክ ቤት ቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ በማስተላለፍ ኢትዮጵያ ሄዶ ከአገር ውስጥ የእርዳታ እህል በመግዛት ወደ አፋር ክልል ያቀናው የልዑኳን ቡድን ሳመራ ከተማ በመደረስ እርዳታውን ነገ እንደሚያከፋፍል ገለፀ። 40% የሚሆነው በእርዳታ የተሰበሰብ ገንዘብ በ eyezonethiopia.com ላይ በተሰራው የእርዳታ ማሰሳበስቢያ ድረ ገፅ ላይ ገቢ መሆኑን ባለፈው ባጠናቀርነው ሪፖርት ላይ ተዘግቧል።
የልዑካኑ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ቅድስት ብርሃኑ በውስጥ መስመር እንደገለፁት ዛሬ ማምሻውን ሰመራ ከተማ የገቡ ሲሆን በነገው እለት ለ800 አባወራዎች የሚሆን 200 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት፣ 80 ኩንታል ሩዝ፣ 2400 ሊትር ዘይት የሚለግሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለ200 ቤተሰቦች 5 ፍይሎችን የሚያበረክቱ መሆኑን ገልፀውልናል።
በልዑካኑ ቡድን እቅድ መሰረት እረዳታውን በወሎ እና በአፋር ለተጎዱ ወገኖች ማከፋፈል ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ስናገኝ ለንባብ እናበቀዋለን።.
No comments:
Post a Comment