በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 27 ይወስዳሉ
********************
በ2013 የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት ፈተና መወሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ተፈራ አብራርተዋል።
የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ሁለተኛ ዙርም በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ፈተናው በሰላም መጠናቀቅ እንዲችል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።
Students who did not take the 12th grade national exam due to security concerns will take the test from January 24 to 27
********************
The Academic Assessment and Examinations Service announced that students who did not take the Grade 12 National Examination in the areas where the security crisis occurred in 2013 will be administered from January 24 to 27, 2014.
Tefera Feisa, Deputy Director General of the Service, said 58,936 students will take the exam in the second round.
Tefera said students who could not pass the exam due to security concerns in Amhara, Oromia and Benishangul-Gumuz states will take the exam.
He recalled that the first round of the 12th grade national examination was completed without any problems and that various activities are underway to end the second round peacefully.
He called on the public and other stakeholders to play their part in ensuring that the exams are conducted peacefully.
He heard them in amazement
በይድነቃቸው ሰማው
No comments:
Post a Comment