የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለ35 ህፃናት የገና በዓል ስጦታ አበረከተ
*********************
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ35 ህፃናት ስጦታ አበረከተ።
ጽህፈት ቤቱ እነዚህን ህፃናት በቋሚነት በማገዝ እንደሚያሳድጋቸውም ተገልጿል።
ስጦታው የተበረከተላቸው በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ስር የሚታገዙ ህፃናት ለእያንዳንዳቸውም የትምህርት ቁሳቁስ፣ የምግብ የአልባሳት ድጋፍን ጨምሮ የ1ሺህ ብር ስጦታ ተከርክቶላቸዋል።
መርሐግብሩ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ሳይነጠሉ ባሉበት ሆነው እንዲደገፉና ወደ ጎዳና ህይወት የሚገፏቸውን ችግሮች መቀነስን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን 320 ህፃናትን እየደገፉ ይገኛሉ ተብሏል።
ይህም ሰፊውን ችግር በትብብር ለማለፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው ነው የተገለፀው።
በፋሲካ አያሌው
The Prime Minister's Office presents Christmas presents to 35 children
*********************
The Prime Minister's Office donated Christmas presents to 35 children.
It is stated that the office will support these children on a regular basis.
The children, who were donated by Mary Joy Ethiopia, received 1,000 birr each for their school supplies, including food and clothing.
The program aims to support children living in isolation from their families and to reduce the burden of street life.
As a result, all ministries, in collaboration with Mary Joy Ethiopia, are supporting 320 children.
It is said that this will go a long way in overcoming the problem.
At Easter

No comments:
Post a Comment