Shop Amazon

Monday, January 3, 2022

The community has donated over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr in kind to the Defense Forces

ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብና ከ971 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ አድርጓል
********************

ለአገር መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ከ971 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ በህዝቡ መደረጉን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኀብረተሰቡን ድጋፍ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ አንድ በመሆን ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በተግባር አሳይተዋል ብለዋል።

የህልውና ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ እስካሁን ድረስ ለሰራዊቱ 971 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ከህዝቡ መደረጉን ተናግረዋል።

ይህም ኢትዮጵያዊያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት በተግባር ያረጋገጠ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

ለሰራዊቱ ገቢ ማሰባሰቢያ በተከፈተው የባንክ አካውንት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡   

"ይሄን መግለጫ እስከምሰጥበት ጊዜ ድረስ 2 ቢሊዮን 41 ሚሊዮን 155 ሺህ 16 ብር በመከላከያ ሚኒስቴር ማዕከል በተከፈተው 1000421912134 አካውንት ቁጥር ገቢ ተደርጓል" ብለዋል።  

በ6800 አጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያም ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ነው የተናገሩት።    

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ በተግባር እያሳየ ያለውን ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
The community has donated over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr in kind to the Defense Forces
 ********************

 The Ministry of Defense said over 2.4 billion birr in cash and over 971 million birr has been provided to the public so far.

 State Minister for Defense Martha Luigi said in a statement that Ethiopians have shown solidarity with the army.

 He said 971 million birr has been provided to the army so far.

 He said this confirms the Ethiopians' partnership with the Defense Forces.

 He said over 2.4 billion birr cash has been donated to the army's bank account.

 "As of this writing, 2 billion 41 million 155 thousand 16 birr has been deposited in the account number 1000421912134 opened at the Ministry of Defense," he said.

 He also mentioned that he has supported more than 200,000 citizens with 6800 text messages.

 He said more than 500 million birr has been collected.

 ENA also called on the Ethiopian people to continue their support for the army.

No comments:

Post a Comment