ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው አብርሆት ሁለገብ ቤተ መፃሕፍት ዛሬ ይመረቃል
****************************************
በአዲስ አበባ 4 ኪሎ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው አብርሆት ሁለገብ ቤተ መፃሕፍት ዛሬ ይመረቃል፡፡
በ19 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቤተመፃሕፍቱ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑ 10 ቤተ-መፃሕፍት መካከል መሆኑ ተነግሮለታል።
ቤተመፃሕፍቱ በ4 ወለሎቹ 1.4 ሚሊዮን መፃሕፍትን መያዝ የሚችል 1.5 ኪ.ሜ መደርደሪያ እንዳለው ተገልጿል፡፡
ቤተመፃሕፍቱ ከ240 ሺህ በላይ መፃሕፍትና 300 ሺህ ጥናታዊ ፅሁፎችን የያዘ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
የህፃናት ማንበቢያ እንዲሁም ማየት ለተሳናቸው አንባቢዎች በቂ የብሬይል መፃሕፍት አቅርቦት ያለው መሆኑም ልዩ ያደርገዋል፡፡
ዘመናዊ ካፍቴሪያና የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ስምንት የመፃሕፍት መሸጫ ሱቆች፣ አምፊ ቲያትርና መጫወቻ ቦታዎችንም ያካተተ ነው፡፡
በተጨማሪም ደህንነቱ የተጠበቀ በአንዴ 115 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ የያዘ ነው።
ቤተ መፃሕፍቱ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚመረቅ ይሆናል።
The Enlightenment Library, built at a cost of over 1.1 billion birr, will be inaugurated today
*******************************************
The lighthouse, built at a cost of over 1.1 billion birr in Addis Ababa, will be inaugurated today.
The 19,000-square-meter library is said to be one of the top 10 libraries in Africa.
The library has a 1.5 km shelf with 1.4 million books on four floors.
The library contains more than 240,000 books and 300,000 articles.
What makes it special is the fact that there are enough Braille books for children's reading and for blind readers.
It also has a modern cafeteria and meeting rooms, eight bookstores, an amphitheater and a playground.
It also has a secure parking lot that can accommodate 115 cars at a time.
No comments:
Post a Comment