አመራሩ በተገኘው ድል ሳይኩራራ በቀጣይ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ፈተናዎች እንዲዘጋጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ
******************
የፌደራል ተቋማትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲያካሂዱ የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ።
በዘመቻ ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በተገኙ ድሎች፣ በታዩ ውስንነቶችና በቀጣይ ስለሚኖረው አቅጣጫ ለሦስት ቀናት ውይይት ሲካሄድበት የቆየው የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ግምገማዊ ሥልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በውይይታቸው በጦርነት የሚገኝ ድልን በአግባቡ መምራት ከጦርነቱ በኋላ ለሚመጣ መረጋጋትና ሰላም እንዲሁም ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ሂደት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አስምረውበታል፡፡
በዘመቻውም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ድል ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የህልውና ዘመቻው ያስከተለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ አሳዛኝና የሀገር እዳ ቢሆንም ሂደቱ ግን በርካታ ትሩፋቶችን እንዳስገኘ አመራሩ መገምገሙ ተመልክቷል፡፡
ተናብቦና ተቀናጅቶ በአንድ አመራር ለአንድ ዓለማ የመስራት አቅም፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ሁለንተናዊ ህዝባዊ ተሳትፎና ተደጋግፎ ችግሮችን በጋራ መሻገርን እንዳስገኘ አመራሮቹ በግምገማ አዘል ስልጠናቸው ማረጋገጣቸው ተመልክቷል፡፡
አመራሮቹ ከድሎቹ ጋር የታዩና በቀጣይም ሊኖሩ ስለሚችሉ መልካም እድሎችና ዝንፈቶች በትኩረት ገምግመዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የመጀመሪያው ምእራፍ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸው ለዚህም ላቅ ያለ ተሳትፎና አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል።
በተገኘው ድል ሳንኩራራ በቀጣይ ሊያጋጥሙን ለሚችሉ ፈተናዎች ተግተን መዘጋጀት እንደሚገባንም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶች ለመጠገን የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስምረውበታል፡፡
በየደረጃው ያለው አመራርም በጦርነቱ ጫና የደረሰበትን የብልፅግና ጉዟችንን ለማስቀጠል ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በዘመቻው የተገኘውን የኅብረ ብሔራዊ አንድነት ስሜት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ እንድንጠቀምበት ጥሪ አቀርባለሁ ማለታቸውን ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Prime Minister Abiy Ahmed urged the leadership to be prepared for the challenges ahead
******************
Federal institutions and senior officials of the Addis Ababa City Administration concluded their discussions on current national issues.
The three-day evaluation training of the senior leaders of the Federal and Addis Ababa City Administration, which was held during the three-day discussion on the achievements, shortcomings and future direction of the campaign for national unity, ended today.
In their discussions, the senior leaders stressed the importance of leading the way to victory in the war, which is crucial for the post-war stability and peace-building process.
He affirmed that Ethiopia and Ethiopians have won the campaign.
Despite the tragic loss of life and property caused by the campaign, the process has yielded many benefits, the administration said.
It has been observed that the leadership's ability to work together for a common purpose, national unity, inclusive public participation and mutual support has helped to overcome common problems.
The leaders carefully considered the pros and cons of the victories.
He thanked Ethiopians for their contribution to the successful completion of the first phase of the National Unity Campaign, which was attended by Prime Minister Abiy Ahmed.
He also emphasized the need to be prepared for the challenges ahead.
He said joint efforts should be made to repair Ethiopia's political and economic divisions.
He stressed that the leadership at all levels must fulfill its historic responsibility to continue the prosperity of the war-torn country.
According to information obtained from the Government Communication Service, Ethiopians have called on the people to use the spirit of national unity gained during the campaign to rebuild the war-torn areas and ensure our overall prosperity.
No comments:
Post a Comment