የአለም የሳቅ ንጉሱና የጊስቡክ የአለም ሪከርድ ባለቤቱ የበላቸው ግርማ ህይወት አደጋ ላይ ነው እንድረስለት ።
ታዋቂው የአለም የሳቅ ንጉስና የደግነት አንባሣደር፣ በጊነስ ቡክ የተለያዩ የአለም ሪከርዶች ባለቤት የሆነው ማስተር በላቸው ግርማ ባጋጠመው የጭንቅላት እጢ ሆስፒታል ገብቶ ቀዶ ጥገናውን በተሳካ ሁኔታ ቢያጠናቀቅም አሁንም ቢሆን ህይወቱ አስጊ ደረጃ ላይ ነው። የተሻለ ህክምና ያለበት ሀገር ሄዶ ህክምና ያገኝ ዘንድ ሁላችንም ልንረዳው ይገባል።
ይህ ከከምባታ ምድር የፈለቀው ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሀገሩን በአለም መድረክ ላይ ብዙዎች በማይሳካላቸውና ከባድ በሆነው የአለም ድንቃድንቅ ተግባራት በሚመዘገቡበት Guines Book of World ላይ በተደጋጋሚ ሪከርዶችን በመስበርና ስሙን እና ሀገሩን በተደጋጋሚ ሰዓት ያስጠራ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነው።
ሆኖም ግን አሁን በበሽታ ተጠቅቶ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ፤ ስለዚህ ይህን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመርዳትና ለማገዝ ቅዳሜ ህዳር 5/2013 በSky Light Hotel ከቀኑ 9:00 ሠዓት ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያና የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ሊደረግለት በአብርሃም ግዛዉ ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይካሄዳል።
ስለዚህ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ ዘመድ አዝማዱ ፣ ጓደኞቹ ፣ አድናቂዎቹ ፣ የመንግስት አካላት ፣ ባለሀብቶች እና ሌሎችም መርዳት የምትፈልጉ ወገናቹን ታግዙና ትረዱት ዘንድ በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000058068277 ማስተር በላቸዉ ግርማ ብላችሁ መርዳት ትችላላችሁ እሱን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0911244101 ወይም 0912374014 ይደዉሉ::
በአክብሮት እንጠይቃለን።
#ሼር በማድረግ መልዕክቱን ለሁሉም ያድርሱት
The majestic life of the King of Laughter and the world record holder of Belachew Girma is in jeopardy.
The world-renowned laughter and benevolent ambassador, Guinness Book of World Records, has successfully undergone surgery on a brain tumor, but his life is still in danger. We all need to help him get to a better country and get treatment.
Born in Kembata, he is a proud Ethiopian who broke his record in the Guinness Book of World Records, one of the most unsuccessful and difficult events in the world.
But now he is sick and bedridden; Therefore, to help and support this proud Ethiopian, a fundraising and arts event will be held at the Sky Light Hotel on Saturday, November 5, 2013 at 9:00 AM hosted by Abraham Gizaw Entertainment.
Therefore, relatives, friends, admirers, government officials, investors and others who want to help, both at home and abroad, can help him by contacting Oromia Cooperative Bank Account No. 1000058068277.
We respectfully ask.
# Share the message with everyone
No comments:
Post a Comment