ከጣሊያን ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት ሁለተኛ ዙር የሽኝት ፕሮግራም በቶሪኖ ተካሄደ
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለዳያስፖራው ያቀረቡትን ግብዣ ተቀብለው በጋራ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት በዝግጅት ላይ ለሚገኙ በጣሊያን ቶሪኖ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ኢትዮጵያ በዓይነት እና በገንዘብ ሀገሩን የሚደግፍ እና አንዳንድ ምዕራባውያን በሀገሩ ላይ ለማድረግ የሚፈልጉትን ጫና እና ጣልቃ-ገብነት በድፍረት የሚታገል ጀግና የዳያስፖራ ኮሚኒቲ አላት ብለዋል።
ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከጊዜያዊ ችግሮቿ ቶሎ ለመላቀቅ አይተኬ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
“እናንተ ሀገር እና ወገኑን ከዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ለመታደግ የምትዘምቱ ዘማቾች ናችሁ፤ ስለሆነም ጉዟችሁ እስከዛሬ ታደርጉት ከነበረው ጉዞ የተለየ መሆን አለበት።” ሲሉም ወደ ሀገር ቤት ለመጓዝ ለተዘጋጁት ወገኖች ተናግረዋል።
“በምትይዟቸው ሻንጣዎች የድጋፍ ቁሳቁሶችን ቅድሚያ ስጡ፣ ብራችሁ በሕጋዊ መንገድ ብቻ መመንዘሩን አረጋግጡ፣ በጦርነቱ የተጎዱትን ከቤተሰብ እኩል ጎብኙ፣ በአጠቃላይ በሚኖራችሁ ቆይታ እና በምታደርጉት እንቅስቃሴ ለሀገርና ወገን ድጋፍ በሚያስገኝ እንዲሁም የሀገራችንን ገፅታ በሚገነባ መልኩ ይሁን” ሲሉም አደራ ማለታቸውን ሮም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዘማች የዳያስፖራ አባላት በበኩላቸው መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሠረት ወደ ሀገር ቤት በመግባት የደረሰውን ጥፋት በአካል በመመልከት በመልሶ ግንባታው የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሄዱ ገልጸዋል።
ወደ ሀገር በሚሄዱበት ጊዜም የተለያዩ መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁሶች ይዘው ለመሄድ መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት።
A second round of repatriation program for Diaspora members from Italy was held in Turin
***********************
A reception was held for Ethiopians and Ethiopians of Ethiopian descent in Turin, Italy, who were preparing to enter the country together in response to Prime Minister Abiy Ahmed's invitation to the Diaspora.
Ambassador Demitu Hambissa, who was present at the event, said Ethiopia has a heroic Diaspora community that supports the country in kind and financially and boldly fights the pressure and interference of some Westerners in the country.
He said Ethiopia has an important role to play in getting rid of its temporary problems.
"You are the ones who are fighting to save the country and its people from many challenges; So your journey should be different from what you have been doing so far. ” He told those who were preparing to travel home.
"Priority should be given to luggage, ensure that your money is spent only legally, visit the victims equally as a family, during your stay and in your activities in a way that is supportive of the country and the country and builds the image of our country," according to the Ethiopian embassy in Rome.
Campaign members of the Diaspora, for their part, said they would go to the country and play their part in rebuilding the dam at the invitation of the government.
He also said that they are ready to carry various medicines and medical supplies on their way home.
No comments:
Post a Comment