Shop Amazon

Tuesday, January 4, 2022

West Gondar Zone High Court sentenced three brothers to 18 years in prison each on charges of kidnapping.

ፍርድ ቤቱ ሰው የማገት ወንጀል የፈጸሙ ሶስት ወንድማማቾችን በ18 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጣ
*******************

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰው የማገት ወንጀል ፈጽመዋል ያላቸውን ሶስት ወንድማማቾች እያንዳንዳቸውን በ18 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጣ።

የፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አበበ ማስሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ወንድማማቾቹ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

“ወንድማማቾቹ በመተማ ወረዳ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓም በግምት ምሽት 4 ሰዓት ላይ የማሽላ ምርት ወቅተው አውድማ በመጠበቅ ላይ የነበሩ የ14 ዓመት ታዳጊ ህፃንና አንድ ሌላ ግለሰብ ላይ የእገታ ወንጀል በመፈጸማቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል” ብለዋል።

ለጊዜው ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ወንጀሉን የፈፀሙት 1ኛ ተከሳሽ መልኬ መካሻው የጦር መሳሪያ በመያዝ፣ 2ኛ ነጋ መካሻውና 3ኛ ተከሳሽ ታከለ መካሻው የተባሉ ወንድማማቾች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ግለሰቦቹ ተበዳዮችን እጃቸውን አስረው በጫካ በማቆየትና ለጊዜው 50 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው ተቀብለው ለሌላ አጋቾች አሳልፈው መስጠታቸው መረጋገጡን ገልፀዋል።

ከታዳጊ ህፃኑ ጋር የታገተው ግለሰብ ከ3 ቀን ቆይታ በኋላ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓም በግምት ከሌሊቱ 8:00 ሾልኮ በማምለጥ እራሱን ማዳን እንደቻለ ተናግረዋል።

አጋቾቹ ታዳጊ ህፃኑን ደብቀው ከማሰቃየታቸው በላይ በድጋሜ ከቤተሰቦቹ 160 ሺህ ብር ተቀብለው እንደለቀቁት ማስረጃ መረጋገጡን አብራርተዋል።

ወንድማማቾቹ ወንጀሉን ከፈፀሙ በኋላ ለጊዜው ከአካባቢው ቢሰወሩም ፖሊስ ባደረገባቸው ክትትል ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው ባለሙያው አስረድተዋል።

“አቃቢ ህግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በወንድማማቾች ላይ የመሰረተውን ክስ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል መቅጫ 1995/590 ሐ ተላልፈው በመገኘታቸው ጥፋተኝነታቸውን አረጓግጧል” ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባስቻለው ችሎት ጥፋተኛ ባላቸው ሶስት ወንድማማቾች ላይ እያንዳንዳቸውን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉን ባለሙያው አስታውቀዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ ፍርድ ቤቱ  በወንጀሉ ተሳትፈዋል የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ ለፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
The court sentenced three brothers to 18 years in prison for kidnapping
 *******************

 West Gondar Zone High Court sentenced three brothers to 18 years in prison each on charges of kidnapping.

 The court's public relations expert, Abebe Masre, told ENA that the brothers had been convicted of the charges.

 "The brothers were fined for kidnapping a 14-year-old boy and another person who were waiting for a threshing floor during a sorghum harvest on November 30, 2014 in Metema Woreda," he said.

 He said the first defendant, Melke Mekashaw, and Nega Mekashaw, and the third defendant, Takele Mekashaw, were armed with their accomplices.

 He asserted that his confession had been obtained through torture and that his confession had been obtained through torture.

 The hostage-taker managed to escape by escaping around 8:00 pm on December 3, 2014, after a three-day stay.

 He explained that the abductors not only tortured the child but also took 160,000 birr from his family and released him.

 The brothers disappeared from the area after committing the crime, but were arrested and charged on December 9, 2014, according to the expert.

 "The zonal high court, which heard the prosecution's case against the brothers on the basis of human and documentary evidence, found them guilty of violating the 1995/590C Criminal Code," he said.

 The court sentenced three brothers to 18 years in prison each, the expert said.

 According to the expert, the court ordered the arrest of the other suspects in connection with the crime and brought them to justice.


No comments:

Post a Comment