Saturday, April 26, 2014

አደራ ዲያስፖራዎች ይህንን ቢዚነስ ቢዝነስ ነው ብላችሁ ኢትዮጵያ ይዛችሁት እንዳትገቡ

አደራ ዲያስፖራዎች ይህንን ቢዚነስ ቢዝነስ ነው ብላችሁ ኢትዮጵያ ይዛችሁት እንዳትገቡ

ነገሩ ቱ ሌት (too late) ነው። ግን ጀስት (just) ለመናገር ያክል ነው ። አንድ የማውቀው ሱቅ አለ ገበያው የደራ ነው:: ደንበኞች በየቀኑ በቃ ወጣ ገባ ይላሉ ። ልክ የቤንዚን ማደያ (gas station) ይመስል ሁሉም  ብልቃጡን ይዞ ይሰለፋል:: የሳምንት ቀለቡን ሊሽምት። ይህ በአሁኑ ወቅት  የአሜሪካን የህክምና ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። ስሙ የኤሌክትሮኒክስ ሲጋራ (Electronics Cigarette)  ይባላል። ልክ ጋያ ወይም ሲሻ በትንሹ ብልቃጥ እንደ ማጨስ ነው። 

  ይህንን ሲጋራ ብዙዎቹ የሚያጨሱበት ዋናው ምክንያት ማጨስ ማቆም  ወይም መቀነስ እምቢ ብሏቸው ይህንን እንደ አማራጭ መንገድ ወስደውት ነው። ታዲያ በየቀኑ የማገኘው  ከሱቁ የሚሰራ ሲጋራ የተለመደውን እኛ የምናውቀውን   የሚያጨስ  ልጅ አለ።ልጁ እንደ ነገረኝ ይሀ ሲጋራ የሚሞላ ፈሳሽ (liquid) ሲኖረው እንድ ግለሰቡ ምረጫ ኒኮቲን (nicotine) የተባለው ንጥረ ነገር ይበዛል ወይም ያንሳል። አብዛኞች በትንሹ ይጀምሩና ወደታች ከመሄድ ይልቅ አላሰማቸው ሲል ወደላይ የሄዳሉ ወይም ብዙ ያጨሳሉ። ያም ማለት ከዚህ በፊት ከሚያጭሱት በላይ ስለሚያጨሱ እራስ ምታት ይይዛቸውና በላዩ ላይ መደበኛውን ሲጋራ ሲያጨሱ የባሰ አጫሽ ሆነው ቁጭ። 
ታዲያ ከዚያ የሚሰራውን ልጅ ግን ሁሌ መደበኛ ሲጋራ  ሲያጨስ የማየውን ልጅ ለምን እሱ ለሰው እየሸጠ እራሱ እንደማያጭስ ጠየቅሁት። ልጁም እንዲህ አለኝ። እኔ አለርጅክ (allergic) ነኝ አለ። 

የህ ሲጋራ የሚሞላ ሲሆን የተለያዬ ጣም (flavors)  አለው ለምሳሌ አናናስ፣ሜንታ፣ ብርቱካን በቃ የፈለጉት ጣእም። ታዲያ ልጁ ሲንገርኝ ለነሱ የሚላክላቸው ድፍድፍ (concentrate) ሲሆን እነሱ በርዘው ፣ ከልሰው፣ ጨምረው ጨማምረው ነው የሚሸጡት። ታዲያ ያ የኒኮቲን ጭማቂ/ድፍድፍ በጣም ጠንካራ ሰለሆነ ልጁ እንደ ነገረኝ አፉን ልክ እንደ ቀዶ ጥገና ባላሙያ ሸፍኖ ነው የሚሰራው። ግን ያ አፉን የሚሽፍንብት  ማስክ (surgical mask)  በቂ ስላልሆነ ፈሳሹ ቆዳውን ሲንካው በቃ እከክ ያስመስልበታል ታዲያ ልጁ በጣም ስለሚጠየፈውና ስለሚመው  አጫሸ በመሆኑ ብቻ  እሱ የሚያጨሰው መደበኛ ሲጋራ (regular cigarette) ነው። ታዲያ እንደ ልጁ አገላለጥ ኤሌክትሮኖክስ ሲጋራ ኬሚካል ነው። ገና ጥናቶች አልውጡም, ቢወጡም ለጋዎች ናቸው  አንድ ቀን ግን ብዙ ሰው በዚህ ኬሚካል ሰለባ እንደሚሆን አልጠራጠርም። ታዲያ ዲያስፖራ ይህንን መርዝ ለዚያውም ቻይና የተሰራ ነው የሚሆነው አገራችን ይዛችሁ ህዝቡም እንዳትጨርሱት። ከተቻላችሁ ዶሮ አርቡ ፣ ከብት አድልቡ፣  የሹራብ ፋብሪካ ትከሉ፣ሙዝ ብርቱካን እርሻ መስርቱ፣  but not Electronic Cigarette .አደራ ሲያጌጡ ይመለጡ እንዳይሆን::እንተዛዘን!
 


No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.

የቦ ታክስ

ለዲያስፓራ አባላት በሙሉ እንዲሁም አሁን ኢትዮጵያ ላላችሁ። የአሜሪካ ታክሳችሁን ካላችሁበት ሆናችሁ እንድታሰሩ ነገሮችን ሁሉ አናስተካክላለናል። ያልተሰራ የታክስ ውዝፍ (Back Tax)፣ መስተካከል ያለበት ታክስ (Amendment) እንችላለን። የዚህ አመት ታክስ እና ሌሎችንም እንሰራለን።በViberም ሆነ Whatspp ይደውሉልን። ስልክ ቁጥራችን 619 255 5530 ነው ። YebboTax info@yebbo.com Yebbo.com

Translate

Do you need Ethiopian Power of Attorney where your agent can preform several crucial tasks on your behalf? Such as adoption proceedings, buying movable or immovable properties, paying tax, represent you in governmental and public offices and several others tasks with our your physical presence? If your answer is yes get the Ethiopian Power of Attorney or YEBBO now on sale

Shop Amazon

Call Yebbo

የቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ፣ ለ25 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያካበተው የእናንተው በእናንተው። ከምሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የውክልና አገልግሎት መስጠት የኢትዮጵያ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት የቢጫ ካርድ የማውጣት አገልግሎት የታክስ አገልግሎት መስጠት (የትም የኢትዮጵያ ግዛት ይኑሩ) የጉዞ ወኪል የትርጉም ስራ አገልግሎት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 619-255-5530 ይደውሉ።