Shop Amazon

Thursday, May 29, 2014

አዲስ አበባ አሎምፒክ 2022? Addis Ababa Olympic 2022?

ራሽያ ለ2013 ሶቺ ኦሎምፒክ (Sochi Olympics 2013)  ያወጣችውን ወጪ ሰምተው የ2022 ኦሎምፒክ ለዘጋጀት የተሳፉት አሮች በፍራቻ አፈገፈጉ:: 




ባለፈው የክረምት ኦሎምፒክ (ሶቺ ኦሎምፒክ) ላይ ራሽያ ያወጣችውን  62 ቢሊዩን ዶላር አይተው የ2022ን ኦሎምፒክ ለማዘጋ አሰፍስፈው ሲጥብቁ የነበሩ አገሮች ነፍሴ አውጭኝ እሩጫ በመሸምጠጥ ከኦሎምፒክ አዘጋጅነት አመለጡ። እንደ ተንታኞች አባባል ይህን አይንት ሽንፈት ለኦሎፒክስ ኮሚቴ ሲያጋጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው የበጋው ኦሎምፒክ ሎሳንጀለስ ላይ የዛሬ ሰላሳ አመት ገደማ ሲካሄድ ነበር። በዚያን ወቅት ኦሎምፒክ የሚያዘጋጅ ጠፍቶ ሎሳንጀለስ ብቻ ፈቃደኛ በመሆኗ ለኦሎምፒክ የወጣው ወጪ በጣም ዝቅተኛ ሲሆን ትርፉ ግን የትየለሌ ነበር። ያን ትርፍ ሲዩ ነበር ሌሎች አገሮችም ለማዝጋጀት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የነበረው። አሁን ግን ራሽያ 62 ቢሊዮን ዶላር ($62,000,000,000) ስታወጣ ሲመለከቱ "ጎመን በጤና" ብለው ቁጭ ብለዋል። ታዲያ የ2022ን ኦሎምፒክ ደጋሽ ከጠፋ የመጣብንን እኛው መቻል ነው። ታዲያ አዲስ አበባ አሎምፒክ 2022  ሊሆን ነዋ?  አፈርን በረዶ ነው ብለናል  ብለናል፣ ብለናል ቃ ምን ሊያመጡ::

Addis Ababa Olympic 2022?

No comments:

Post a Comment