Shop Amazon

Thursday, May 29, 2014

የጉግል ሹፌር አልባ ወይም ሹፌር የለሽ መኪና ኢትዪጵያ ቢገባስ?

የጉግል ሹፌር አልባ ወይም ሹፌር የለሽ መኪና ኢትዪጵያ ቢገባስ?
"አር ዩ ኪዲንግ ሚ /Are you kidding me? "አለ ፈረንጅ። ባሁኑ ወቅት በሙከራ ላይ ያለው ሹፌር አልባ መኪና ኢትዮጵያ ቢገባ እራሱ ሳስበው ያስቀ ኛል። በኔ ግምት መኪናው ሃያ አራት ሰዓት ተገትሮ የቀራል እንጂ መንገድ የሚለቅለይ የለም። ለምን በሉኝ? በቅርቡ አገር ቤት ሄጄ ያየሁት ሁኔታ በመኪናና በእግረኛ መካክለ ያለው መናናቅ ነው።  መኪናው ሲከንፍ እንኳን እግረኛ ጉንዳን ያለ አይመስለውም፣ መንገደኛው ደግሞ መንገድ ሲያቋርጥ እንኳን መኪና መንገዱ ላይ እርግብ ያዬ አይምስለውም። ሁሉም ተሻሽተው ሾፌር አንግቱን አስቶጥቶ መንግደኞችን በቁጣ አስለቅቆ መንገደኛ ደግሞ መኪና አህያ ይመስል መኪናን በቡጢ ጀርባውን ዥልጦ ሁሉም ተሰዳድበው ፣ ተጫጩኸው ነው የሚለያዩት። ፒያሳ፣ መርካቶ እና አራት ኪሎ ላይማ ከመኪና በሞቶ እጥፍ እግር ይፈጥናል። ታዲያ ይታያች ሁ ማነው ለሾፌር አልባ መኪና መንገድ የሚለቅለት? "ቆመህ ቅር አሉ።" አቶ ጉግል ከዚህ ፕሮጄክት ላይ ኢትዮጵያን ለቀቅ አድርጋት  የጆፒኤሱ (GPS) ፕሮጄክት ይበቃናል

No comments:

Post a Comment