Shop Amazon

Thursday, May 15, 2014

ሳንድያጎን ለምን እሳት ያጠቃዋል?

ሳንድያጎን ለምን እሳት ያጠቃዋል?


ሳንድያጎን (San Diego) በአካልም ሆን በምስል ላያችሁት ውበቷ ወደር የሌለው ቆንጆ ከተማ ነው። የተፈጥሮ ቁንጅናዋ ከተለያዩ ከተሞች ለመጎብኘትም ሆን ለማዬት የመጡትን ቋሚ ነዋሪ አድርጎ በማስቀረት የታወቀች ከተማ ናት። ሳንድያጎ በሁለት ይከፈላል አንዱ ሳንድያጎ አውራጃ ወይም ካውንቲ (county) የሚሉት ሲሆን ሌለው ደግሞ ሳንድያጎ ከተማ (city) ናት። ሳንድያጎን ካውንቲ ወይም አውራጃ ከአራት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሚኖርበት ትልቅ አውራጃ ነው። ሳንድያጎ ከተማ ደግሞ በውበቷ አሉ ከሚባሉ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ደረቷን ለሰላማዊ (Pacific Ocean) ውቅያኖስ አጋልጣ የተቀመጠች ባህ ዳር ላይ ያለች ከተማ ናት። ሳንድያጎ ከተማ ለመስፋት ያላት እድል በጣም ጠባብ ነው። ወደ ደቡብ (south) እንዳይሰፋ የሜክሲኮ አገር አለ, ወደ ምእራብ (west) እንዳይሰፋ ደግሞ የሰላማዊ ውቅንያኖስ አለ ስለዚህ ህዝቡ ያለው አማራጭ ወደ ሰሜን እና ወደ ሰሜን ምስራቅ ነው። ከሳንድያጎ ከተማ ወጣ በተባለ ቁጥር ደግሞ  በጣም ትቅጥቅ ያለ በተራሮች የተከበበ ጫካ ነው። አብዛኛው ጫካ በህግ እንዳይቆረጥ የተጠበቀ  ደን ነው። ይህ  አርንጓዴ  ደን በቂ ዝናብ ሲያገኝ ለከተማው ውበት ነው ፣ ግን በዚህ አመት  በአለም ደረጃ በተፈጠረው የአለም የአየር ንብረት መናጋት (Global Worming)  ሳንድያጎም ሆነ ካሊፎርንያ ውስጥ በቂ ዝናብ ስላልነበር ያሁሉ ደን ልክ እንድ ጭራሮ ደርቆ ትንሽ እሳት ነው የሚጠብቀው። ታዲያ አንዱን ትንሽ እሳት ሲንካው ሌላው እንደ ጭድ ይጋያል። የሚገርመው ህዝቡ ያለበትን ቦታ ስለሚወደው ዛሬ ቢቃጠል እንኳ ነገ ሌላ አዲስ ቤት ይገነባል። ሳንድያጎ ያላት የአየር መጠን ወይም ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋር ስለሚምሳስል ብዙዎች ይወዱታል። በጣም ከባዱ ኑሮ ውድ መሆኑ ብቻ ነው።

ታዲያ አብዛኛአ አብሻ የሚኖረው ከከተማው መሃል ስለሆንና ከተማው ውስጥ ብዙ ደን ስለሌለ እስካሁን ሁሉም ስላም ነው። ከከተማ ወጣ ብለው የሚኖሩትንም እየደወልን ጥይቀናል እስካሁን ሰላም ነው። ግን በሌሎች ነዋሪዎች ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።

No comments:

Post a Comment