የኢትዮጵያ ህፃን ብልጥ፣ ተማሪ፣ ተመራማሪ፣ ፈጣሪ እና ታታሪ ነው። ይህንን የተረዳሁት ያው አሜሪካ አገር ወይም ሌላው የደገ አገር ያሉትን ህፃናት አይቼ ነው። ለምሳሌ ባደጉት አገሮች አንድ ህፃን ከሆድ ከወጣ ጀምሮ አሻንጉሊት በሻንጉሊት ነው። ሲተኛ በአሻንጉሊት ፣ አልጋው አሻንጉሊት፣ የሽንት ቤት መቀመጫው አሻንጉሊት, ዳይፕሩ (Dipper)አሻንጉሊት በቃ ሁሉም አሻንጉሊት ነው።
እኛ ስናድግ ምግባችን የናታችን ጡት (breastfed) ፣ አልጋችን የናታችን ጀርባ እና አንቀልባ ሙዚቃችን ደግሞ የእናታችን ወይም የህቶቻችን የወንድሞቻችን እሽሩሩ ሙዚቃ ነው።ከዚያ ትንሽ አደግ ብለን ጥርስ ካዎጣን ነገሩ አለቀ ነው። አያስጨንቀንም። ጤነነታችን ደህና ይሁን እንጂ የበሉትን በልተን የጠቱትን ጠጥተን በቃ ያራሳችንን መጫዎቻ እራሳችን ሰርተን ፏ ብሎ መኖር ነው
ከዚህ ከ west (የአደገው አገር) ልጆች ያላቸው ያሻንጉሊት ማአት አይጣል ነው። በቃ አንዳንዴ ቤት አጣቦ ሳይጠቀሙበት የሚጣለው ሆድ ይፍጀው ነው። ሕጻናቱ አንዱን ጨብጠው ሌላውን ተጫውተው ሳይጥግቡ ሌላ በላይዩ ላይ ይደረባል። በቃ አንዳንዴ ወይ የሰበራል ወይ ውጭ ተጥሎ ይረሳል። በመሃል የሚጠቀሙት የቻይና የአሻንጉሊት ፋብሪካዎችና በየ አገሩ ያሉ የ አሳንጉሊት ሻጮች ናቸው። የባለ ሱቆች ብልሃትማ አይጣል ነው። ያን መከረኛ ወላጅ ልክ እንደ አሻንጉሊት ይጫወቱበታል። በቃ አንዴ ገና (Christmas) ልደት (Birthday) ሌላም ሌላም እያሉ ሳይወድ በግዱ ያስገዙታል። ታዲያ ያ ሁሉ የአሻንጉሊት ጋጋታ ለህጻኑ እውቀት መዳበር ምን ያክል እንደሚረዳ ትንሽ ግር ያሰኛል። ያው የተለመደው የቀለም አይነት፣ ቅርጽ ወይም ድምጽ መማር ነው ። ለዚያውም ለማስተማሪያ ተብለው ታስቦባቸው የተሰሩ አሻንጉሊቶች አሉ። ብታምኑ ባታምኑም ህጻናቱ በብዛት አይዎዷቸውም። ሁሌም ዝንባሊቸው ከሚያብረቀርቀው ቅራቅንቦ ላይ ነው።
ያገራችን ልጅስ? ያሁኑን አላውቅም እኔ ሳድግ ግን አሻንጉሊት/መጫወቻ የገዛልኝ ስው አልነበረም። እኔም አስቤምው አላውቅም። ሰው ቢገዛልኝ የምመኘው ከረሜላ (candy) ብቻ ነበር። ግን የምፈልገው መጫወቻ ወይም አሻንጉሊት ነበረኝ። ያው እራሴ ሰርቸው ነው። እዚህ አገር ሪሳይክሊንግ (recycling) እንደሚሉት ለመሳሌ መኪና ከተለያዩ ነገሮች ይሰራል። የሚያስፈልጉ ጠንካራ ሽቦ፣ ባዶ የጫማ ቀልም ቆርቆሮ እና ለመሪ የሚሆን ዱላ እንዲሁን አንዳንዴ ጎማው ከሽቦ ከተሰራ ውፍርት እንዲኖረው ጨርቅ ወይም አሮጌ አንሶላ ነው።ከዚያ መኪናው ይሰራል። የመኪናው አሽከርካሪ እና ተሳፋሪዎች ከተፈለጉ ከጭቃ ይሰራሉ። ያ ነው ፈጠራ። ታዲያ ያን የሰራነውን መኪና አብረን ከመንደር ለጆች ጋር ስንነዳው አቤት ያለው ደስታ!

No comments:
Post a Comment