Shop Amazon

Monday, June 9, 2014

ክላሲካል እና የኢንስቱርመንታል ልዩነት Classical vs. Instrumental

ክላሲካል እና የኢንስቱርመንታል ልዩነት Classical vs Instrumental
ክላሲካል እና የኢንስቱርመንታል ልዩነት መችም ይህ የእንግሊዝ እንግሊዘኛ(British English)  ይሆናል በቃ እኛ ሁሉት የተለያዩ ነግሮችን አዟዙረን እናዋራለን። ይህም ክላሲካል እና ኢንስቱርመንታል የሚሉትን ሙዚቆችን ነው። በተለምዶ ክላሲካል ማለት በመሳሪያ ብቻ የሚጫዎት ማለት ነው ብለን ደምደመናል:: ግን በጣም የተሳሳት አንጋገር ነው። ክላሲካል ማለት የቆዬ የድሮ የጥንት ማለት ነው እንጂ በመሳሪያ የሚጫዎት ማለት አይደለም። አንድ ሙዚቃ ወደ ክላሲካል ወገን ለመቀላቀል ቢያንስ ቢያንስ  ከመቶ አመት በላይ እድሜ ሊኖረው ይገባል አነስ ከተባለ ደግሞ  ሃምሳ አመት በላይ። ለምሳሌ ክላሲካል ተብለው ከሚጠሩት ከያንያን መካከል  ሞዛርት(Mozart)፣  ሃንዲ(Haydn)፣ ሪተን(Britten)፣ ራምስ (Brahms)፣ በይቶበን(Beethoven)፣ ሹበት(Schubert)፣ ኮዳል (Kodaly)፣ ይገኙበታል። ታዲያ በዚህ አይነት ከሄድን በሃገራችን ውስጥ ልክ እንድ ክላሲካል ተብሎ የሚጠሩት ገናናው የያሬድ ስራዎች ናቸው ማለት  ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ኢንስትሩመንታል ማለት የዘፋኙ ድምጽ ሳይገባ መሳሪያውን ብቻ መጫዎት ነው። ያም ማለት የዛሬ መቶ አመትም ሆነ ያዛሬ ሳምንት የተጫዎቱን ሙዚቃ ለዚህ እጩ ነው። ያም የዘፋኙ ድምጽ ሳይገባ የምንሰማው ሙዚቃ ክላሲካል ሳይሆን ኢኑስቱርመንታል ነው። ታዲያ ሌላ ጊዜ ክላሲካል ክፈቱልኝ ሳይሆን ኢንስቱርመንታል ክፈቱልኝ ነው ማለት አለባችሁ። ልዩነታቸው በቁርጥ ስጋና በቋንጣ መካከል እንዳለው ነው።
አደራ አልሰማንም እንዳትሉ። ይህንን የምታውቁ ደግሞ እስከዛሬ እኔ ስ ሰሳት የት ነበራችሁ ?
ታዲያ ይህን ሁሉ ስል ካለ ምክንያት አይደለም። ትናንት የሆን ቆንጆ ቦታ ሄጄ ይህንን ክላሲካል ቋቅ እስኪለኝ ኮምኩሚያለሁ። ቪዲዮውንም አካፍላችሗለሁ ጠብቁ.





No comments:

Post a Comment