Not use what but some reason there is some kind of dispute between Team Teddy and Team Coke over the release of this World Cup African special collaboration. We are less than one day away from the starting bell of World Cup 2014. Well why the wait let us share what we have. Music should not boundaries
"አስከመጨረሻው የዓለም ዋንጫ መከፈቻ ዕለት የመጨረሻ ሴኮንድ ድረስ እንጠብቃለን፡፡
ሰኔ ግንቦት 23 2006 አለአግባብ እንዳይለቀቅ በተደረገው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ አስመልክቶ ያለንን አቋም በመግልፅ መግለጫ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡
ምንም እንኳን መግለጫውን በድረ ገፃችን ላይ አትመን ለማውጣት ከመወሰናችን በፊት ጉዳዩን በተመለከተ ለኮካ ኮላ እና ወኪሉ ለሆነው ማንዳላ ቲቪ አስቀድመው እንዲያውቁት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ ላለፉት በርካታ ወራቶች ተደጋግሞ ሳያቋርጥ የገጠመን በመሆኑ የሚያስደንቀን አልሆነም፡፡
እኛን ባስደነቀን መልኩ “ታዲያስ መጋዚን” በተሰኘ ድረ ገፅ ላይ ባለፈው ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ኮካ ኮላ ያወጣውን መግለጫ ለመመልከት የቻልን ሲሆን ምንም እንኳን ይህው መግለጫ በቀጥታ ለእኛ ያልደረሰን ቢሆንም ለክቡራን አድናቂዎቻችን በመግለጫው ውስጥ የተካተቱት ጭብጦች ምንም ዓይነት የውል፣ የፍሬ ነገር እና የህግ መሰረት የሌላቸው መሆኑን ማብራራቱ እና መግለፁ አግባብነት ይኖረዋል ብለን አምነናል፡፡
መግለጫው ቴዲ አፍሮ ከኮካ ኮላ ጋር እንዴት እና ለምን ግብ ግንኙነት እንዳደረገ እንደሚከተለው በማተት ይጀምራል፤ “ቴዲ አፍሮ አፍሪካ ባለው የኮካ ሰቱዲዬአችን የመጣው የኮካ ኮላ ቅጂ የሆነውን “ዓለም የኛ ነች” የተሰኘውን የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ ልዩ ዓይነት የሆነውን ኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ለማሰቀረፅ በታቀደ ግብ ነበር” ይላል መግለጫው፡፡
ይሁን እንጂ መግለጫው ማን “እንዳመጣው” እና ምርጫውንም እንዳደረገ አያመለክትም ወይም አይገልፅም፡፡ በመግለጫችን ላይ እንዳብራራነው ለኮካ ፕሮጄክት ወደ እኛ በመቅረብ ምርጫውን በማድረግ ተነሳሽነቱን የወሰደው አቶ ምስክር ሙሉጌታ ከመሆኑ በተጨማሪ ይህው ስው ከኮክ ሰቱዲዮ ጋር በማገናኘት ከኮካኮላ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ሊሚትድ ወኪል ከሆነው ከማንዳላ ቲቪ ጋር ውል እንድንዋዋል አድርጓል፡፡
ከአቶ ምስክር እና ከማንዳላ ቲቪ ጋር ኮካ ኮላ በቅደም ተከተል የአሰሪ እና ሰራተኛ እንዲሁም የወኪል እና የወካይ ግንኙነት ያለው ቢሆንም በመግለጫው ላይ አንዳችም ዓይነት ግንኙነት ስለመኖሩ ከማስተባበሉ አልፎ በመሄድ “ከቴዲ አፍሮ ጋር የተደረገው ውል ማንዳላ ሊሚትድ በተሰኘ እና መቀመጫው ናይሮቢ በሆነ አዘጋጅ ተቋም “በ3ኛ ወገን” በኩል የተፈፀመ ነው” በማለት በአፅንኦት ገልጾ ራሱን ከነበረው ትስስር ነጥሏል፡፡
3ኛ ወገን የሚለው ቃል …..የስምምነት ወይም የግብይት…. ወገን ያልሆነ እና አልፎ አልፎ ከስምምነቱ ወይም ከግብይቱ ውጪ የሆነ ወገን ተብሎ ይገለፃል፡፡ እንደ ኮካ ኮላ መግለጫ ከሆነ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የኮካ ኮላ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ምስክር ሙሉጌታ እና ለኮካ ኮላ በኮካ ስቱዲዮው በኩል ሙዚቃ ነክ ንብረቶችን ለማዘጋጀትና ለማስተዋወቅ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያቀርብለት ወኪሉ ማንዳላ ቲቪ ኮካ ኮላ ከአደረገው ስምምነት እና ግብይት እንዲሁም በመግለጫው ላይ “የኮካ ሰቱዲዬአችን” በሚል ፍንትው ባለ አገላለፁ ካመለከተው ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸው ባይታወሮች ናቸው፡፡
አቶ ምስክር እንደ ተቀጣሪ ሰራተኝነታቸው እና ማንደላ ቲቪም እንደ ወኪልነቱ ልዩ ልዩ ሙዚቃ ነክ ንብረት አገልግሎቶች ለማከናወን በመዋዋል በማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ኮካ ኮላ ምትክ እና ፋንታ ህጋዊ ተግባራታቸውን ሲፈፅሙ ልክ ዋና መስሪያ ቤቱ አትላንታ ለሚገኘው እና መግለጫውን እንዳወጣው የኮካ ኮላ ተወካይ አንድ ዓይነት የሆነ የህግ ችሎታ/አቋም እና ውጤት አላቸው፡፡
ይህ በራሱ ተቀጣሪ ሰራተኛ እና በወኪሉ መካከል ያለውን የፍሬ ነገር እና የህግ ትስስር ሙሉ ለሙሉ በመካድ ኮካ ኮላ ባወጣው መግለጫው ላይ “ሶስተኛ ወገን” የሚል ከቶም አግባብነት በሌለው ቃል ተክቶ ራሱን ከማናቸውም ግንኙነት ለማራቅ ምክሯል፡፡ ይህም ሁኔታ በቅዱስ መፅሐፍ ላይ ጲላጦስ የፈፀመውን ፈፅሞ “ከደሙ ንፁህ ነኝ” ያለውን ጥቅስ ያስታውሰናል፡፡
ይህ ክብርን የሚያቃልል እና የሚነሳ መግለጫ የሰው ልጅን፣ የሁሉም አድናቂዎቻችንን እና የኮካ ኮላንም ደንበኞች ጭምር ዕውቀት፣ አእምሮ እና ግንዛቤ የሚገዳደር እና የሚፈታተን ነው፡፡ ይህም አድራጎቱ ቆሜለታለሁ ከሚለው የኩባኒያው የስነ ምግባር መርሆዎች ማለትም ከመልካም ስብእና፣ ታማኝነት፣ የህዝብ አመኔታ እና አሌኝታነት ጋር የሚፃረርም ነው፡፡
በእርግጥ ኮካ ኮላ ከቴዲ አፍሮ ጋር ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት ከሌለው እንግዲያውስ በአጠቃላይ መግለጫውን ለማውጣትና ከሁሉም በላይ ደግሞ ቴዲ “ለአደረገው ጥረቱ ሙሉውን” የተከፈለው ስለመሆኑ እና “የተሰራው ሙዚቃ የማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ኮካኮላ ንብረት ሆኗል” በማለት አፅንኦት ሰጥቶ ለማረጋገጥ ለምን አሰፈለገው?”
አሳዛኙ ነገር ላለፉት ወራቶች ከኮካ ኮላ እና ከማንዳላ ቲቪ ጋር ስናደርግ በነበረው የቃል እና የፁሁፍ ግንኙነቶች ተመሳሳይና አስደንጋጭ ጎጂ ተግባራቶችን ስንቀበልና ስናስተናገድ ቆይተናል፡፡ እነኚህ ድርጊቶች ከቅን ልቦና የመነጩ ወይም የዕውቀት ማነሰ ውጤት ናቸው የሚል ዕምነት የለንም፡፡ ይልቁንም ሆን ተብሎ የሚፈፀም ፍፁም ተቋማዊ የማናለብኘነት አድራጎት ነው፡፡
ይህም ቢሆን ግን ራሱን በሚያከበር ኢትዮጵያዊ በሚመጥን ትዕግስት፣ ትህትና እና አክበሮት በጉጉት መለቀቁ እየተጠበቀ ያለውን ሙዚቃ ወይም ሊለቀቅ የማይችልበትን ምክኒያት አስከመጨረሻው የዓለም ዋንጫ መከፈቻ ዕለት የመጨረሻ ሴኮንድ ድረስ እንጠብቃለን፡፡"
No comments:
Post a Comment