ጋዜጠኛነት ክብር ያለው ስራ ነው። ጥሩ ጋዜጠኛ ማለት እውነትን የሚወድ ማለት ነው።

ጋዜጠኛነት ክብር ያለው ስራ ነው። ጥሩ ጋዜጠኛ ማለት እውነትን የሚወድ ማለት ነው። 
በእኔ እይታ ሁለት አይነት ጋዜጠኞች አሉ። እርስዎ ጋዜጠኛ ከሆኑ የትኛው ምድብ እንደሆኑ እራስዎን ይጥይቁ።

ምድብ አንድ  እውነት አዳኝ ፥ ይህ ጋዜጠኛ ማለት ስራው እውነትን በገባችበት ገብቶ የሚያወጣ እውነተኛ ጋዜጠኛ ነው። ስራው በውሸት ቆሻሻ ተሸፍና መተንፈሻ አጥታ በወሸት ጭቃ ተለውሳ የተደበቀችውን እውነት አድኖ፣ አጥቦ አጽድቶ ወልውሎ ለእይታ ያበቃታል። አንዳንዴም እውነትን ለማጋነን ትንሽ ጌጥ ጣል ጣል ያደርግባታል። ያ ማስፋት ይባላል

ሁለተኛው ጋዜጠኛ ደግሞ እውነት ገዳይ ውሸት  አዳኝ
፥ የዚህ ጋዜጠኛ ስራ እውነተን በውሸት ቆሻሻ እንዳትታይ መደበቅ ነው። ስራው ሁሉ እውነትን በውሸት ተራራ ሸፍኖ ለእይታ እንዳትበቃ ማድረግ ብቻ ነው። ስራው ህዝብን ማደናገር፣ እርስ በርሱ ማናከስ፣ አንዱን በውሸት አሞክሾ ሌላውን የውሸት ጭቃ መቀባት ነው።

ታዲያ በጋዚጠኝነት ሙያ የተሰማሩ ወይም የሚሰማሩ ከሆን እርስዎ ስራዎ እውነትን አድኖ ለንባብ ማብቃት ወይስ እውነትን ገድሎ ውሸትን ማወደስ?

Comments

Popular posts from this blog

Birhanu Nega scapped death

What company has copoun in Groupon

የአሜረካው ስታር ባክስ ኩባንያ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን በነፍስ ወከፍ 50ሺ ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ