Shop Amazon

Sunday, July 26, 2015

Obama is in Ethiopia. His brother who is living in Ethiopa greeted him

Air Force One landed at ADD (Bole) international airport  on Sunday Ethiopian time. It was a rainy day. According to Ethiopian Broadcasting Service English program (live) Obama was greeted by senior  member Ethiopian Government, the Ethiopia prime minster and his older brother. Yes, for our surprise Mr. President has an older brother who is living in Ethiopia a boarder city called Moyale which is near to Kenya



According to this Amharic article/blog Obama has one older brother lives in Ethiopia in a border town called Moyale which is near Kenya. His name is Oke and he is 59 years old. He said he born in Kenya a place called Oma Kogilo from his father Husien Barack and his mother Rochi Nyang and moved to Ethiopia when he was 2 years old because his mom was divorced and remarried an Ethiopian business man called Alemayehu. After he born his father Mr. Barack has eight children . In 1961 when Obama was born in Hawaii he came to see hm (where) with his aunt. When his father was graduated from University of Hawaii he sent his an invitation letter and he attended the graduation. Also he added he attended the wedding ceremony of Obama's mother. The story need farther investigation
የ ባራክ ኦባማ ወንድም ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራሉ።
===========================

አርባ አራተኛው የ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በ አባታቸው ሁሴን ኦባማ በኩል የተገኙ ስድስት ወንድም'ና አንድ ሴት እንዳላቸው የታወቀ ቢሆንም አሁን ከ ኢትዮጵያ ሙያሌ አካባቢ የተሰማ ድምፅ ግን
"የለም እኔ ኡኬ ኦባማ የሁሉም ታላቅ ወንድም ነኝ" የሚል ሆኗል
ኡኬ ኦባማ ሙያሌ ውስጥ በድለላ ስራ የሚተዳደሩ መሆናቸውን ገልፀው የባራክ ኦባማ ታላቅ ወንድም ስለመሆናቸው ሁሉን ነገር በማስረጃ ይናገራሉ
"አባታችን ሁሴን ኦባማ ስኮላር ሺፕ አግኝቶ ወደ አሜሪካ ሀዋይ ከማቅናቱ በፊት በ 1956 እኔን ከ እናቴ ሮቺ ቲማ ኒያንግ ኦማ ኮጊሎ በምትባል አነስተኛ መንደር ውስጥ ወልድዋል እናቴ እኔ የሁለት አመት ህፃን ሳለሁ ከ አባቴ ጋር ተጣልታ ወደ ኢትዮጵያ መጣች እዚህም አለማየሁ ተምትም የተባለ ትውልዱ ሀዋሳ የሆነ ነጋዴ አግብታ መኖር ጀመረች" ሲሉ ማስረጃቸውን ማቅረብ የጀመሩት ኡኬ
እሳቸው ከተወለዱ በኋላ አባታቸው ሁሴን ስምንት ልጆችን እንደ ወለዱ ይናገራሉ። እኤአ በ 1961 ዓ.ም የ አሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሲወለድ ከ እናቱ እህት ማለትም ከ አክስታቸው ቼሙ ጋር በመሆን ለመጠየቅ መምጣታቸውንም ጨምረው የሚገልፁት የ 59 ዓመቱ ኡኬ አባታቸው ሁሴን ኦባማ ከ ሀዋይ ዩኒቨርስቲ በ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ሲመረቁ የ "ኢንቪቴሽን"ወረቀት ልከውላቸው የምርቃቱ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ'ና በድጋሚም የ ወንድማቸው ባራክ ኦባማን እናት ስታንልይ ዱንሀምን ባገቡበት ጊዜ ለሰርግ ወደ ቺካጎ ሄደው እነደ ነበር ይገልፃሉ
"እርግጥ ነው እኔ አሁን የ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ነኝ ብዬ ብናገር ማንም አያምነኝም ብዙ ሰዎች ኦባማን ትመስላለህ ከማለት ውጪ ምንም የስጋ ወንድሙ ስለመሆኔ ምንም አያውቁም እውነታው ግን አባቴ ከነበሩት ዘጠኝ ልጆች ማለትም ማሊክ ኦባማ፣ አውማ ኦባማ፣ባራክ ኦባማ ማርክ ኒድሳንዶ ኦባማ፣ዴቪድ ኒድሳንዶ ኦባማ፣ኦቦ ኦባማ፣ በርናንድ ኦባማ'ና ጆርጅ ኦባማ ከሁሉም ታላቅ የሆንኩት እኔ ኡኬ ኦባማ ነኝ" በማለት ይናገራሉ አክለውም
"አባታችን ሁሴን ገና በወጣትነቱ በ አርባ ስድስት አመቱ መሞቱ እንጂ ሁላችንንም በ አንድ ላይ ለማገናኘት ታላቅ እቅድ ነበረው ግን ምን ያደርጋል ሞት ቀደመው" በማለት እንባ እያቀረረቸው ገልፀዋል
ከባራክ ሁሴን ኦባማ ጋር ተገናኝተው የተነሷቸው ፎቶች በሙሉ በወቅቱ ካሜራውን ይዞ የነበረው ሰው ፎቶ ለማንሳት ጀማሪ በመሆኑ ሁሉንም ፎቶዎች እንዳቃጠላቸው ምሬታቸውን በቁጭት ሳይሸሸጉ ከተናገሩ በኋላ እለተ ሰኞ ወንድማቸው አዲስ አበባ ሲመጣ ከሙያሌ ተገዘው በመሄድ ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው ልክ ኬንያ እንዳለችው እህታቸው አውማ ኦባማ በሞቀ ሰላምታ መቀበል ባይችሉም የ እራት ፕሮግራሙን ግን በ እርግጠኛነት በቴሌቭዥን ቁጭ ብለው እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።
"እንዴ ለምን?" ሲባሉ
"ሂዱ ከዚህ የተመሳሰለ ሁሉ ወንድም'ና እህት ነው ያለው ማን ነው? ወረኛ ሁላ
ይልቅ እስከ አሁን በባዶ ላስለፈለፋችሁኝን የበርጫ ገፍትሩልኝ'ና ልሂድ ሲሉ ተማፅነዋል።
@ቴዎድሮስ ጌታሁን

ይህ የ አለማችን ትፅእኖ ፈጣሪውን ፕሬዝዳንት መምጣት በጉጉት ለሚጠብቁ ሁሉ ሰበር ዜና ነው።

No comments:

Post a Comment