Wednesday, November 25, 2020

በማይካድራ ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኙ

በማይካድራ ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኙ

***************** 

በማይካድራ ከተማ አብነት እና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ ቦታዎች በሕወሓት ጨፍጫፊ ቡድን ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኝተዋል።

56 ዜጎች በአንድ ሥፍራ የተገኙ ሲሆን፣ አስከሬናቸው የውኃ ጉድጓድ ውስጥ የተከተተ ሰለባዎች መኖራቸውም ተረጋግጧል።

ሕወሓት ከጅምላ ግድያው በኋላ የዘር ማጥፋቱን ወንጀል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለመደበቅ የግድያውን ሰለባዎች ከከተማዋ አርቆ መደበቁን ከጥቃቱ የተረፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

ሕወሓት ከጭፍጨፋው በተጨማሪም በከተማዋ የሚኖሩ አማራዎች በስጋት እንዲሸሹ የማድረግ ትልም እንደነበረውም ተገልጿል። 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መረጃ ጨፍጫፊው ሕወሓት በትንሹ 600 ሰዎች እንደገደለ እና በየቦታው የተገደሉ ሰዎች ስለሚገኙ ቁጥሩ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል።

በገዳይ ቡድኑ ሕይወታቸው ያለፈ ንጹሐን ዜጎች አስከሬን በክብር እንዲያርፍ መደረጉንም አብመድ  ዘግቧል።

An additional 74 people were found dead in Maikadra

 *****************

 An additional 74 people were killed by the TPLF in the rural areas of Mekadra, Abnet and Central Mewcha.

 56 citizens were found at one location, and the bodies of the victims were found buried in a well.

 Survivors say the TPLF has hidden the victims far from the city to hide the genocide from the international community after the massacre.

 In addition to the massacre, the TPLF also sought to intimidate Amharas living in the city.

 The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) said in a statement on Monday that the TPLF had killed at least 600 people and that the number could be higher.

 The bodies of innocent people who lost their lives in the assassination were also honored, Abmed reported.

No comments:

Post a Comment