****************
የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ገለፀ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ጋር በብራሰልስ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።
ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሀገር መሆንዋን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ በሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው ለንፁሃን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥበትን መንገድ ለማመቻቸት በመንግሥት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
አቶ ደመቀ በበኩላቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ታሳቢ በማድረግ እና ነባራዊ ሁኔታውን በማጥናት ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የሚደረግበትን አግባብ አስረድተዋል።
ንፁሃን ዜጎች ለከፋ ቀውስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እና ሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
The European Union (EU) has said it is not interested in interfering in Ethiopia's internal affairs
****************
The European Union (EU) has said it is not interested in interfering in the country's internal affairs.
Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs Demeke Mekonnen met with EU Commissioner for Disaster Management Janice Lenarchich in Brussels to discuss current affairs in Ethiopia.
He said the EU is not interested in interfering in the country's internal affairs.
"Ethiopia is a strategic partner for the union," he said. He called on the government to intensify its efforts to provide humanitarian assistance to innocent people.
Demeke, for his part, explained how humanitarian assistance can be achieved by taking into account international human rights conventions and studying the current situation.
According to information obtained from the Office of the Deputy Prime Minister, the government will continue to intensify its efforts to ensure that innocent people are not exposed to the worst of the crisis and that humanitarian assistance is readily available.
No comments:
Post a Comment