Thursday, November 26, 2020

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ጋር በሰላምና ደህንነት መስኮች የነበራቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ጋር በሰላምና ደህንነት መስኮች የነበራቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ 
*****************

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሰላምና ደህንነት መስኮች እንዲሁም ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ። 

የብሄራዊ  መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን  ጥሩነህ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ ጋር በዛሬው ዕለት ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። 
     
በውይይታቸውም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ ጋር  ትብብሩን በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአቅም ግንባታ ሥልጠና ዘርፍ ይበልጥ ተባብረው ለመሥራት ማቀዳቸው ተገልጿል።
 
የብሄራዊ  መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በውይይቱ  ወቅት እንደገለጹት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ የሚደረግለትን ሁሉን አቀፍ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ድጋፎች በመጠቀም ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና ከሥሩ በመንቀል ረገድ ያላት አቋም ጠንካራ መሆኑን የጠቀሱት የእስራኤል የሞሳድ ዳይሬክተር ጀነራል ሚስተር ዮሴፍ ኮ`ን ልዩ መልዕክተኛ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ የህዝቦች የጋራ ጠላት የሆነውን ሽብርተኝነትን በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል ሞሳድ ከኢትዮጵያ አቻ የመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በትብብር እንደሚሰራና ድጋፉንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። 
በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ኃላፊው በእስራኤል የሞሳድ ዳይሬክተር ጀነራል ሚስተር ዮሴፍ ኮ`ን  ስም ለተቋሙ የተላከውን የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶች የፊት ጭምብል፣ ቬንቲሌሽን፣ ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገልግሉ አልባሳቶችን ድጋፍ ለብሄራዊ  መረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስረክበዋል። 

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በባህል፣ በሃይማኖት፣ በታሪክ እና በፖለቲካው ዘርፎች የረጅም ጊዜ ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በመረጃና ደህንነት ዘርፉ ያላቸውን ተቋማዊ ግንኙነት እያጠናከሩ መምጣታቸውን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመልክቷል።      

Agree to further strengthen cooperation with the National Intelligence and Security Service and the Israeli intelligence agency Mossad in the fields of peace and security
 *****************

 The National Intelligence and Security Service (NISS) and the Israeli intelligence service Mossad have agreed to strengthen cooperation in the areas of peace and security, as well as counter-terrorism.

 Director General of the National Intelligence and Security Service, Temesgen Tiruneh, met with the head of the Mossad Office in Ethiopia and the Horn of Africa today.

 During the meeting, the National Intelligence and Security Service (NISS) said it plans to strengthen cooperation with Mossad in the fight against terrorism in the Horn of Africa, as well as in the field of technology and capacity building.

 Director General of the National Intelligence and Security Service, Temesgen Tiruneh, on the occasion said the National Intelligence and Security Service (NISS) will work to ensure peace and security in the Horn of Africa, using the capacity building and technology support provided by Mossad.

 "Mossad will work with the Ethiopian Intelligence and Security Agency (IAEA) to work together to prevent terrorism, which is a common enemy of the people of Ethiopia and the Horn of Africa.  You have verified.

 Temesgen Tiruneh, Director General of the National Intelligence and Security Agency (NISS), on behalf of the Mossad Director General of Ethiopia and the Horn of Africa, Mr. Youssef Koen, on behalf of the Mossad Director of Israel.

 Ethiopia and Israel have established long-standing ties in the fields of culture, religion, history and politics, and have recently strengthened their institutional ties in the information and security sector, the National Intelligence and Security Service (NISS) said in a statement.

*Machine Translation

להסכים לחיזוק נוסף של שיתוף הפעולה עם שירות המודיעין והביטחון הלאומי וסוכנות הביון הישראלית מוסד בתחומי השלום והביטחון
 *****************

 שירות המודיעין והביטחון הלאומי (NISS) ושירות הביון הישראלי מוסד הסכימו לחזק את שיתוף הפעולה בתחומי השלום והביטחון, כמו גם נגד טרור.

 מנכ"ל שירות המודיעין והביטחון הלאומי, טמסגן טירונה, נפגש היום עם ראש משרד המוסד באתיופיה וקרן אפריקה.

 במהלך הפגישה הודיע ​​שירות המודיעין והביטחון הלאומי (NISS) כי הוא מתכנן לחזק את שיתוף הפעולה עם המוסד במאבק בטרור בקרן אפריקה, כמו גם בתחום הטכנולוגיה ובניית יכולות.

 מנכ"ל שירות המודיעין והביטחון הלאומי, טמסגן טירונה, אמר בהזדמנות כי שירות המודיעין והביטחון הלאומי (NISS) יפעל להבטחת שלום וביטחון בקרן אפריקה, תוך שימוש בבניית יכולות ותמיכה טכנולוגית הניתנת על ידי המוסד.

 "מוסד יעבוד עם סוכנות המודיעין והביטחון האתיופית (IAEA) בכדי לעבוד יחד למניעת טרור, שהוא האויב המשותף של תושבי אתיופיה וקרן אפריקה.  אימתת.

 טמסגן טירונה, מנכ"ל סוכנות הביון והביטחון הלאומית (NISS), מטעם מנכ"ל המוסד של אתיופיה וקרן אפריקה, מר יוסף קון, מטעם מנהל המוסד בישראל.

 שירות המודיעין והביטחון הלאומי (NISS) אמר כי אתיופיה וישראל יצרו קשרים ארוכי שנים בתחומי התרבות, הדת, ההיסטוריה והפוליטיקה.


 

No comments:

Post a Comment