የጦር ሀይሎች ጠ/አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመከላከያ ሰራዊታችን የመጨረሻውንና ሶስተኛውን የዘመቻ ምዕራፍ እንዲፈፅም ትዕዛዝ ሰጡ ፡፡
የመከላከያ ሰራዊታችን በሰላማዊ ዜጎች ፣ በቅርሶች ፣ በቤተ እምነቶች ፣ በልማት ተቋማትና በንብረቶች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ጁንታውን ለህግ የሚያቀርብበትን ጥንቃቄ የተሞላው የዘመቻ ስልት መንደፉን አረጋግጠዋል ባወጡት መግለጫ።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የመጨረሻው የዘመቻው ምእራፍ ተጀምሯል።
የተሰጠው የ72 ሰዓት ጊዜ ተጠናቋል፤ ህግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሸው ምእራፍ ላይ ደርሷል። በተሰጠው የ72 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ሰጥተዋል።
ብዙ የትግራይ ወጣቶችም የህወሓትን እኩይ አላማ ተረድተው እጃቸውን ሰብስበዋል። ይህ በመጨረሻው ሰዓትም ቢሆን የተወሰደ ሀላፊነት የሚሰወማው ውሳኔ ህሊና ካለው ፍጡር የሚጠበቅ ውሳኔ ነው።
መንግስት 72 ሰዓት ሲሰጥ አላማው ሁለት ነበር። በአንድ በኩል ዋና ፍላጎቱ ህግ ማስከበር እንጅ ጦርነት አለመሆኑን መግለጥ ነው።
አንደኛው ፣ ጁንታው በሰላም እጁን ለመስጠት ከቻለ ዘመቻውን በማጠናቀቅ ህግን በአነስተኛ ዋጋ ለማስከበር ይቻላል ብሎ ያምናል። ለዚህም ሲባል ተደጋጋሚ እድሎችን ሰጥቶ ነበር።
ሁለተኛው ደግሞ ፣ የህወሓት የጥፋት አላማ ዘግይቶም ቢሆን የገባው አንድም ሰው ከተገኘ ያንን ሰው ለማትረፍ እንዲቻል ነው።
ለህወሓት ጁንታ የተከፈተው የመጨረሻ ሰላማዊ በር በጁንታው እብሪት ምክንያት ተዘግቷል። የጥፋታቸውን አላማ ተገንዝቦ ለሚመለስ ሰው በተከፈተው በር ግን፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሚሊሻ እና ልዩ ሀይል አባላት እጃቸውን እየሰጡ ገብተውበታል።
የመከላከያ ሰራዊታችን የመጨረሻውን እና ሶስተኛውን የዘመቻ ምዕራፍ እንዲፈፅም ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። በዚህ ዘመቻ ለንፁሃን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በህዝባችን ላብ የተሰራችው የመቐለ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።
ቅርሶች ፣ ቤተ እምነቶች ፣ የህዝብ መገልገያዎች ፣ የልማት ተቋማት እና የህዝብ መኖሪያዎች የጥቃት ኢላማ እንዳይሆኑ ሁሉም አይነት ጥንቃቄ ይደረጋል።
የመቐለና የአካባቢው ህዝባችን ትጥቁን ፈትቶ በቤቱ በመቀመጥና ከወታደራዊ ዒላማዎች በመራቅ፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።
November 17, 2013
Commander-in-Chief of the Armed Forces and Prime Minister Abiy Ahmed has ordered the Defense Forces to complete the final and third phases of the campaign.
In a statement, the Defense Forces confirmed that they have devised a prudent campaign to bring the Junta to justice without harming civilians, heritage, religious institutions, development institutions and property.
The full text of the statement is as follows:
The final phase of the campaign has begun.
The 72-hour period is over; The law enforcement campaign has come to an end. Within 72 hours, thousands of Tigray Special Forces and militia members surrendered to the Defense Forces.
Many young people in Tigray, realizing the TPLF's evil intentions, have joined hands. This last-minute decision is a matter of conscience.
When the government gave 72 hours, it had two goals. On the one hand, his main concern is law enforcement, not war.
First, he believes that if the junta can surrender peacefully, it will be possible to complete the campaign and enforce the law at a lower cost. To this end, he has provided numerous opportunities.
Second, the TPLF's destructive intent is to save that person if anyone is found late.
The last peaceful gate for the TPLF Junta has been closed due to Junta's arrogance. But the door is open for anyone who realizes the purpose of their crime and returns; Thousands of Tigray militia and special forces surrendered.
Our defense forces have been ordered to complete the final and third phases of the campaign. In this campaign we take great care of innocent people; The city of Mekelle, built by the sweat of our people, will do its utmost to prevent further damage.
All precautions should be taken to ensure that heritages, denominations, public facilities, public institutions and public housing are not targeted.
The people of Mekelle and its environs disarmed and stayed at home and away from military targets; We urge him to take all necessary precautions.
We call on the people to contribute by reducing the number of Junta members to a minimum.
We want to assure you that our Defense Forces has devised a careful campaign strategy to bring the Junta to justice without harming civilians, heritage, denominations, development institutions and property.
በጥቂት የህወሓት ጁንታ አባላት ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ህዝቡ የጁንታውን አባላት አሳልፎ በመስጠት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጥሪ እናደርጋለን።
የመከላከያ ሰራዊታችን በሰላማዊ ዜጎች፣ በቅርሶች፣ በቤተ እምነቶች፣ በልማት ተቋማትና በንብረቶች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ጁንታውን ለህግ የሚያቀርብበትን ጥንቃቄ የተሞላው የዘመቻ ስልት የነደፈ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
No comments:
Post a Comment